"ሉአላዊነት የሚጸናው በፈተና ሳይወድቁ በመቆም፤ በወጀብ ሳይናወጡ መጓዝ በመቻል ነው" - የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የዒድ አል አድሃ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት

© telegram sputnik_ethiopia"ሉአላዊነት የሚጸናው በፈተና ሳይወድቁ በመቆም፤ በወጀብ ሳይናወጡ መጓዝ በመቻል ነው" - የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የዒድ አል አድሃ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት
ሉአላዊነት የሚጸናው በፈተና ሳይወድቁ በመቆም፤ በወጀብ ሳይናወጡ መጓዝ በመቻል ነው - የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የዒድ አል አድሃ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት - Sputnik አፍሪካ, 1920, 26.05.2026
ሰብስክራይብ

"ሉአላዊነት የሚጸናው በፈተና ሳይወድቁ በመቆም፤ በወጀብ ሳይናወጡ መጓዝ በመቻል ነው" - የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የዒድ አል አድሃ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት

ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ በዛሬ ዕለት ባስተላለፉት መልዕክት፤ ሕዝበ ሙስሊሙ በዓሉን በአብሮነት እንዲያከብር በመጠቆም መልካም በዓል እንዲሆን ተመኝተዋል።

"ሀገር የምትገነባው ከራስ ጥቅም በላይ በሚያስቡ እና ከግላዊ ፍላጎታቸው በላይ ለመፈጸም በቆረጡ ዜጎች ነው። የሚወዱትን ነገር እንኳን ሳይቀር ለመሠዋት ዝግጁ የሆኑ ዜጎች ሲበዙላት ሀገር ትበረታለች። እስማኤላቸውን ለመስጠት የማያመነቱ ዜጎች የሞሉባት ሀገር ጽኑ ናት።

የለመድናቸው፣ የምንወዳቸው፣ የራሳችን ገንዘብ ያደረግናቸው ብዙ ነገሮች ይኖራሉ። ከእነዚህ የሚበልጥ ዓላማ ግን አለ፤ እሱም “ሀገርነት እና ሉአላዊነት” ይሰኛል። ሀገርነት የሚገነባው ከመውሰድ ይልቅ በመስጠት ነው። ሉአላዊነት የሚጸናው በፈተና ሳይወድቁ በመቆም፤ በወጀብ ሳይናወጡ መጓዝ በመቻል ነው።" ሲሉ የበዓሉን ታሪክ መሠረት ያደረገ መልዕክት አስተላፈዋል፡፡

በመግለጫቸው ያነሷቸው ተጨማሪ ጉዳዮች፦

አሁን ያለው የምስራቅ አፍሪካ ቀጣናዊ ተግዳሮትና ሀገራዊ ሁኔታዎችን በማንሳት፤ ሀገር የምትገነባው ከራስ ፍላጎትና ጥቅም በላይ ለሕዝብና ለሀገር ደኅንነት ዋጋ ለመክፈል ዝግጁ የሆኑ ዜጎች ሲኖሯት ነው ብለዋል፡፡

ማኅበራዊ ትዕግሥትና ትብብር ለሀገር አንድነት ወሳኝ መሆናቸውን አጽንኦት ሰጥተዋል።

ዜጎች በበዓሉ ወቅት ማኅበራዊ ግዴታቸውን ከመወጣት ባለፈ ለሀገሪቱ ሰላም፣ ዕድገትና ዴሞክራሲያዊ መብቶች መከበር በ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩን ሙሉ መግለጫ ከላይ ከተያያዘው ምስል ይመልከቱ፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0