ኢትዮጵያ ከውጭ የምታስገባውን የሶላር ምርቶች መጠን በ390% ማሳደጓ ተዘገበ

ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ ከውጭ የምታስገባውን የሶላር ምርቶች መጠን በ390% ማሳደጓ ተዘገበ

በሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ በተከሰተው የእንቅስቃሴ መቋረጥና የነዳጅ አቅርቦት ቀውስ ምክንያት የዓለም የኃይል ገበያ መናጋቱን ተከትሎ ኢትዮጵያ የሶላር የገቢ ምርቶች ላይ የመጠን ዕድገት ማስመዝገቧን የዘርፉ ዓለም አቀፍ ተቋም የሆነው የኢነርጂ ሽግግር ኮሚሽን ያወጣው አዲስ ሪፖርት አመልክቷል።

እንደ ኢትዮጵያ ባሉ በነዳጅ አስመጪ ሀገራት ላይ የትራንስፖርት፣ የምግብና የኢንዱስትሪ ወጪዎችን በከፍተኛ ሁኔታ መጫኑ ዘርፉ ተፈላጊነቱ እንዲጨምር ማድረጉን ሪፖርቱ ጠቁሟል።

በዚህም ይህን ስትራቴጂካዊ ሥጋት ለመቋቋም ኢትዮጵያን ጨምሮ 50 ሀገራት ፊታቸውን ወደ ታዳሽ ኃይል በማዞር የሶላር ምርቶች ግዢያቸውን በከፍተኛ ፍጥነት እያሳደጉ መሆኑን ሪፖርቱን ጠቅሶ የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ኢትዮጵያ ከአንድ ወር በፊት ሚያዚያ 18 ቀን 2018 ዓ.ም የሶላር ኢነርጂ ፋብሪካ አስመርቃለች፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የመረቁት የቶዮ ሶላር ኢነርጂ ሁለተኛው ምዕራፍ፣ ኦርጅን እና ሉሚንቴክ የሶላር ፋብሪካዎች እንዲሁም የኤች.ዜድ ጋዝ ፋብሪካ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0