ኢትዮጵያ ከ118 ዓመታት በኋላ የመጀመሪያውን የንግድ ፖሊሲ አፀደቀች

© telegram sputnik_ethiopiaኢትዮጵያ ከ118 ዓመታት በኋላ የመጀመሪያውን የንግድ ፖሊሲ አፀደቀች
ኢትዮጵያ ከ118 ዓመታት በኋላ የመጀመሪያውን የንግድ ፖሊሲ አፀደቀች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 26.05.2026
ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ ከ118 ዓመታት በኋላ የመጀመሪያውን የንግድ ፖሊሲ አፀደቀች

የሚኒስትሮች ምክር ቤት የሀገሪቱን የንግድ ሥርዓት በዘመናዊ መንገድ ለመምራት ያስችላል ያለውን “የኢትዮጵያ የንግድ ፖሊሲ” በሙሉ ድምፅ አፅድቋል።

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር (የቀድሞ ንግድ ሚኒስቴር) ከተቋቋመ በኋላ የመጀመሪያ የሆነው ፖሊሲ ያስፈልገበትን ምክንያት እንደሚከተለው ተዘርዝሯል፦

የገበያ ክፍተቶችን ለመሙላት፦ የሀገር ውስጥና ዓለም አቀፍ የንግድ ሥርዓትን በአግባቡ ለመምራት፣

የወጪ ንግድን ለማዘመን፦ በግብርና ላይ ብቻ ያለውን ጥገኝነት በመቀነስ የውጭ ገቢን ለማሳደግ፣

ፍትሐዊ አሰራርን ለመዘርጋት፦ የምርት ደህንነትን ለማረጋገጥና ሕገወጥ ውድድርን ለመግታት እና

ኢንዱስትሪዎችን ለማጠናከር፦ የሀገር ውስጥ አምራቾች ምርታማነትና ተወዳዳሪነት እንዲያድግ ለመደገፍ።

“ይህ ፖሊሲ ሀገራችን ለዘመናት ንግድን በተበታተኑ ሕጎች ስትመራበት የነበረውን አሰራርን ከመሠረቱ በመቀየር የሀገር ውስጥና የወጪ ንግድን የተቀናጀ፣ ተገማችና በሕግ ማዕቀፍ ወደሚመራ አስተዳደር የሚያሸጋግር ነው።” ሲሉ የንግድ እና የቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ የፖሊሲውን መጽደቅ አስመልክቶ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ላይ ጽፈዋል፡፡

ፖሊሲው ከዛሬ ጀምሮ ተፈጻሚ እንዲሆን ምክር ቤቱ ወስኗል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0