ሳይንቲስቶች በ3ዲ ፕሪንተር ከተሠራ ዕንቁላል 26 ጫጩቶችን አስፈለፈሉ
14:55 26.05.2026 (የተሻሻለ: 15:04 26.05.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
#viral | ሳይንቲስቶች በ3ዲ ፕሪንተር ከተሠራ ዕንቁላል 26 ጫጩቶችን አስፈለፈሉ
የተለያየ ዕድሜ ያላቸው ጫጩቶች በ3ዲ ፕሪንተር ከተሠራ እና የዕንቁላል ቅርፊት ቅርጽ ካለው መዋቅር ውስጥ ተፈልፍለው ወጥተዋል።
ዓላማው፦ አሜሪካ መሠረቱን ያደረገው ኮሎሳል ባዮሳይንሰስ የተባለው ተቋም፣ በዘር ምህንድስና የተቀየሩ እና ዝርያቸው የጠፋውን የሞአ ወፍ ጫጩቶችን ለማምረት ያለመ ሲሆን፤ ይህም ወደፊት በዚሁ ቴክኖሎጂ በመጠቀም ሌሎች ዝርያቸው የጠፉ እንስሳትን “በሕይወት ለመመለስ” እንደ መጀመሪያ እርምጃ የሚወሰድ ነው።
ተግዳሮቱ፦ የሞአ ወፍ ዕንቁላሎች ከተራ የዶሮ ዕንቁላሎች በ80 እጥፍ የሚበልጡ በመሆናቸው፣ ሌላ በሕይወት ያለችን ወፍ እንደ ተተኪ እናት በመጠቀም ዕንቁላሎቹን እስከሚፈለፈሉ ድረስ ማቆየት የማይቻል አድርጎታል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X