ኢትዮጵያ በቀጣናው በተከሰተው የኢቦላ ስጋት ምክንያት በሁሉም መግቢያ ኬላዎች ላይ ጥብቅ የጤና ምርመራ መጀመሯን አስታወቀች
13:28 26.05.2026 (የተሻሻለ: 13:34 26.05.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ በቀጣናው በተከሰተው የኢቦላ ስጋት ምክንያት በሁሉም መግቢያ ኬላዎች ላይ ጥብቅ የጤና ምርመራ መጀመሯን አስታወቀች
የጤና ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር በኢቦላ ወረርሽኝ ላይ ከፍተኛ የቅድመ ዝግጅትና የጥንቃቄ ሥራዎችን መተግበር መጀመሩን ገልጿል። በዚህ መሠረትም የሚከተሉትን የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን እያከናወነ ይገኛል፦
በሁሉም ዓለም አቀፍ የየብስ መግቢያ እና መውጫ ኬላዎች የልየታ እና የቅኝት ማድረግ፣
በዓለም አቀፍ አየር ማረፊያዎች የተጠናከረ ክትትል፣
የጤና ተቋማት ዝግጁ በማድረግ እንዲሁም የላቦራቶሪ አቅምን በማሳደግ እና
አስፈላጊ የሕክምና ግብዓት አቅርቦት ማጠናከር፡፡
ቫይረሱ ከፍተኛ የስርጭትና የሞት ምጣኔ ያለው ቢሆንም እስካሁን ባለው መረጃ በኢትዮጵያ ምንም ዓይነት በበሽታው የተጠረጠረ ወይም የታመመ ሰው አለመገኘቱ ተገልጿል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X