የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በማዳጋስካር በይፋ ተመዘገበች

ሰብስክራይብ

የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በማዳጋስካር በይፋ ተመዘገበች

የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የአፍሪካ ሀገረ ስብከት እንዳስታወቀው፤ ይህ ይፋዊ መግለጫ የተሰማው በአገሪቱ ውስጥ በሩሲያ ኦርቶዶክስ ካህናት የተመራው የቅዳሴ ሥነ-ሥርዓት በተጠናቀቀበት ወቅት ነው።

በዚህ የጸሎት ሥነ-ሥርዓት ላይ የሩሲያ ጉዳዮች አስፈጻሚ አሌክሲ ቡርያክ፣ የኤምባሲው የሥራ ባልደረቦች እና የአካባቢው አማኞች ተገኝተዋል። በዓሉን በማስመልከት የኦርቶዶክስ መንፈሳዊ መጻሕፍት ለሩሲያ ኤምባሲ ቤተ-መጻሕፍት መበረከቱን የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አስታውቃለች፡፡

ከቅዳሴው በኋላ፣ የአካባቢው የሃይማኖት አባቶች በማዳጋስካር ያለውን የኦርቶዶክስ ተልዕኮ የበለጠ ለማስፋፋት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ለመወያየት ስብሰባ አካሂደዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0