የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ወደ ቻይና ለሚላኩ ምርቶች የወጪ ንግድ ፈቃድ በሁሉም ባንኮች እንዲሰጥ ፈቀደ

© telegram sputnik_ethiopiaየኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ወደ ቻይና ለሚላኩ ምርቶች የወጪ ንግድ ፈቃድ በሁሉም ባንኮች እንዲሰጥ ፈቀደ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ወደ ቻይና ለሚላኩ ምርቶች የወጪ ንግድ ፈቃድ በሁሉም ባንኮች እንዲሰጥ ፈቀደ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 26.05.2026
ሰብስክራይብ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ወደ ቻይና ለሚላኩ ምርቶች የወጪ ንግድ ፈቃድ በሁሉም ባንኮች እንዲሰጥ ፈቀደ

ባንኩ በዛሬው ዕለት ባወጣው መግለጫ እንዳመላከተው፣ ቀደም ሲል ወደ ቻይና ለሚላኩ ምርቶች የወጪ ንግድ ፈቃድ የሚሰጠው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በኩል ብቻ እንዲሆን ተጥሎ የነበረው ገደብ ሙሉ በሙሉ ተነስቷል።

ይህ ውሳኔ የተላለፈው የሀገሪቱን የወጪ ንግድ ዘርፍ ይበልጥ ለማቅለል፣ ተወዳዳሪነትን ለማሳደግ እና ለላኪዎች ምቹና ተደራሽ የባንክ አገልግሎት ለመፍጠር ታስቦ መሆኑ ገልጿል።

በዚህም መሠረት ከዛሬ ጀምሮ ፈቃድ ያላቸው ሁሉም የንግድ ባንኮች ከተለመዱት የወጪ ንግድ እና የውጭ ምንዛሬ መመሪያዎች ጋር በተጣጣመ መልኩ ለደንበኞቻቸው አገልግሎቱን መስጠት እንዲጀምሩ ብሔራዊ ባንክ አሳስቧል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0