‘ለአፍሪካ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሔዎች’፦ ምናንጋግዋ በአፍሪካ ቀን አገር በቀል የፈጠራ ሥራዎች እንዲስፋፉ ጥሪ አቀረቡ

ሰብስክራይብ

‘ለአፍሪካ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሔዎች’፦ ምናንጋግዋ በአፍሪካ ቀን አገር በቀል የፈጠራ ሥራዎች እንዲስፋፉ ጥሪ አቀረቡ

የዚምባብዌ ፕሬዝዳንት በአፍሪካ ቀን ባስተላለፉት መልእክት፤ የአኅጉሪቱ መጻኢ ዕድል በአገር ውስጥ እውቀት እና ሀብት ላይ የተመሠረተ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተው የገለጹ ሲሆን፣ ተቋማት ለአህጉሪቱ ተግዳሮቶች አገር በቀል ምላሾችን እንዲያፈልቁ አሳስበዋል።

ፕሬዝዳንቱ የዚምባብዌ የውሃ ፕሮጀክቶችን የአየር ንብረት መቋቋም አቅምን የማሳደጊያ ማሳያ አድርገው ያቀረቡ ሲሆን፤ የዘንድሮው መሪ ቃል፣ “ዘላቂ የውሃ አቅርቦት እና አስተማማኝ የንጽሕና አጠባበቅ ሥርዓቶችን ማረጋገጥ” ወሳኝ መሆኑን ጠቁመዋል። ውሃ የልማት የሕይወት መሠረት (ደም ሥር) ነው ሲሉም ተናግረዋል።

  ምናንጋግዋ በሚከተሉት የፈጠራ መፍትሔዎች ላይ ኢንቨስትመንት እንዲደረግ ጥሪ አቅርበዋል፦

🟠 የፍሳሽ ቆሻሻ ውሃን መልሶ ጥቅም ላይ ማዋል (ሪሳይክሊንግ)፣

🟠 በፀሐይ ኃይል የሚሠሩ (ሶላር) ሥርዓቶች፣

🟠 ዲጂታል ክትትል እና 

🟠 ውሃን በቁጠባ ለሚጠቀም ግብርና የሚውሉ የድሮን ኢንተርፕራይዞች።

በመጨረሻም አህጉሪቱ ወደ አፍሪካ ኅብረት ‘አጀንዳ 2063’ ለምታደርገው ጉዞ ዚምባብዌያውያን፣ በተለይም ወጣቶች፣ አርበኝነትን፣ ፈጠራን እና ጠንክሮ መስራትን እንዲላበሱ በማሳሰብ ንግግራቸውን አጥቅለዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0