የአፍሪካ ቀን፦ ከዓለም ዙሪያ የተላለፉ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክቶች
የአፍሪካ ቀን፦ ከዓለም ዙሪያ የተላለፉ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክቶች
እ.አ.አ በ1963 የአፍሪካ አንድነት ድርጅት የተመሠረተበትን ዕለት በማስመልከት፣ የተለያዩ የዓለም መሪዎች ለአፍሪካ አገራት ያላቸውን ድጋፍ ገልጸዋል።
ለአፍሪካ መጻኢ ዕድል የተመኙትን አነቃቂ ምኞቶች እና ያቀረቡትን ጥሪዎች ከዚህ በታች ይመልከቱ
አንቶኒዮ ጉተሬዝ፣ የተባበሩት መንግሥታትዋና ጸሐፊ፦ ይህ በዓል የአህጉሪቱን እምቅ አቅም፣ ጥንካሬ፣ ተስፋ እና በዓለም አቀፍ መድረክ ላይ እያደገ የመጣውን ተጽዕኖ የሚያንጸባርቅ ነው።ማሕሙድ አሊ ዩሱፍ፣ የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር፦ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት መመሥረት “ለአንድነት፣ ለነፃነት፣ ለክብር እና ለልማት የምናደርገውን የጋራ ጥረት ማነሳሳቱን የቀጠለ ታሪካዊ የማዕዘን ድንጋይ ነው።”
ቭላድሚር ፑቲን፣ የሩሲያ ፕሬዝዳንት፦ የአፍሪካ አገራት “አስደናቂ ኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ ስኬቶችን” ያስመዘገቡ ሲሆን፣ በዓለም አቀፍ መድረክ ላይም “እያደገ የመጣ ሚና” እየተጫወቱ ይገኛሉ።
አሌክሳንደር ሉካሼንኮ፣ የቤላሩስ ፕሬዝዳንት፦ ሚንስክ (የቤላሩስ መዲና) ከበርካታ የአፍሪካ አገራት ጋር በግብርናው ዘርፍ ለምታከናውናቸው ፕሮጀክቶች ትልቅ ትኩረት ሰጥተዋል።
የቱርክ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፦ የአፍሪካ ቀን የአፍሪካ አህጉርን የሰላም፣ የነፃነት፣ የአንድነት እና የአብሮነት መንፈስ የሚያመለክት ነው።
ኔቱምቦ ናንዲ-ንዳይትዋ፣ የናሚቢያ ፕሬዝዳንት፦ አፍሪካ ከኢኮኖሚ፣ ከአየር ንብረት እና ከሕዝብ ጤና ጋር በተያያዘ እየጨመረ ከመጣው ዓለም አቀፋዊ ጫና አንጻር፣ ለአፍሪካውያን ተግዳሮቶች አፍሪካዊ መፍትሔዎችን በከፍተኛ ሁኔታ መሻት ይኖርባታል።
ኤመርሰን ምናንጋጓ፣ የዚምባብዌ ፕሬዝዳንት፦ የአፍሪካ መጻኢ ዕድል በገዛ እውቀቷ፣ ሀብቷ እና የፈጠራ ብቃቷ የመጠቀም አቅሟ ላይ የተመሠረተ ነው።
ዐቢይ አሕመድ፣ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር፦ "ኢትዮጵያ በዚህ በአንድነት መንፈስ ከሁሉም የአፍሪካ አገራት ጎን ትቆማለች። ከቃል ወደ ተግባር፣ ከምኞት ወደ ዕድገት እንሻገር" ብለዋል።
አብዱላዬ ማይጋ፣ የማሊ ጠቅላይ ሚኒስትር፦ ለሁሉም ሰው “ደስ የሚል የአፍሪካ ቀን” እንዲሆን ተመኝተዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X