የኔቶ አገራት መለያ የሆኑ ማግኔቲክ ፈንጂዎች በሩሲያ ወደብ በቆመች መርከብ ላይ ተገኙ - የፌደራል የደህንነት አገልግሎት

ሰብስክራይብ

የኔቶ አገራት መለያ የሆኑ ማግኔቲክ ፈንጂዎች በሩሲያ ወደብ በቆመች መርከብ ላይ ተገኙ - የፌደራል የደህንነት አገልግሎት

ከቤልጂየም ተነስታ ኡስት-ሉጋ ወደተባለው የሩሲያ ወደብ በደረሰችው መርከብ ላይ የተገኙት እነዚህ ፈንጂዎች፣ በሩሲያ የባህር ክልል ውስጥ ሊገጠሙ እንደማይችሉ የደህንነት አገልግሎቱ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

በጋዝ ጫኝ መርከቧ ላይ ሊሰነዘር የነበረውን የሽብር ጥቃት ማክሸፍን በተመለከተ ከአገልግሎቱ የተገኙ ሌሎች ዋና ዋና ነጥቦች፦

ፈንጂ የተገጠመባትና ከቤልጂየም የመጣችው መርከብ ከኡስት-ሉጋ ተነስታ ወደ ቱርክ ለመጓዝ ቀጠሮ ተይዞላት የነበረ ነው፡፡

ከቤልጂየም በመጣችው መርከብ ላይ በተገኙት በእያንዳንዱ ፈንጂዎች ውስጥ የነበረው የፈንጂ ንጥረ-ነገር ክብደት በግምት 7 ኪሎ ግራም ያህል ነበር፡፡

ፈንጂዎችን ጭና ኡስት-ሉጋ የደረሰችው መርከብ፣ በወደብ ሠራተኞች አድማ ምክንያት በሚል ሰበብ በቤልጂየም ለአንድ ቀን ተኩል ያህል መልሕቅ ጥላ እንድትቆም ተደርጎ ነበር፡፡

የሩሲያ የምርመራ ኮሚቴ ከቤልጂየም በመጣችው መርከብ ላይ ፈንጂዎች መገኘታቸውን ተከትሎ፣ ከተሞከረው የሽብር ጥቃት ጋር በተያያዘ የወንጀል መዝገብ ከፍቶ ምርመራ ጀምሯል።

የደህንነት አገልግሎቱ ይፋ ያደረገው ቪዲዮ “አርሄኒየስ” በተባለችው የጋዝ ጫኝ መርከብ አካል ላይ የተጣበቁትን ፈንጂዎች ያሳያል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0