ኢትዮጵያ ለቀጣዮቹ አምስት ዓመታት የምትተገብረውን የኢ - ሞቢሊቲ ስትራቴጂ እና የአፈጻጸም ዕቅድ ይፋ አደረገች
18:34 25.05.2026 (የተሻሻለ: 18:44 25.05.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ ለቀጣዮቹ አምስት ዓመታት የምትተገብረውን የኢ - ሞቢሊቲ ስትራቴጂ እና የአፈጻጸም ዕቅድ ይፋ አደረገች
በስትራቴጂው ይፋዊ ማስጀመሪያ መርሀ ግብር ላይ የተገኙት የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክ ሚኒስትሩ ዓለሙ ስሜ፣ ኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን እና ለአካባቢ ተስማሚ የሆኑ የትራንስፖርት አማራጮችን በማስፋት ረገድ አበረታች መሻሻሎችን ስለማሳየቷ ተናግረዋል።
ስትራቴጂው ከ2025 እስከ 2030 የሚያገለግል ሲሆን፣ ከአሁን ቀደም የተሰጡ ምክረ ሐሳቦችንና አስተያየቶችን አካቶ በአዲስ መልክ የተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል ሲል የስፑትኒክ አፍሪካ ጋዜጠኛ ዘግቧል።
ዕቅዱን በተመለከተ የበለጠ ለማወቅ ቪዲዮውን ይመልከቱ
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X