የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሬ ፈቃድ እና የሰነድ መክፈያ የማጽደቅ ሥልጣንን ለንግድ ባንኮች ሰጠ
17:48 25.05.2026 (የተሻሻለ: 17:54 25.05.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሬ ፈቃድ እና የሰነድ መክፈያ የማጽደቅ ሥልጣንን ለንግድ ባንኮች ሰጠ
ብሔራዊ ባንኩ ወደ ገበያ መር የውጭ ምንዛሬ ሥርዓት እያደረገ ያለውን ሽግግር ለማጠናከርና የአሠራር ማነቆዎችን በመቅረፍ የንግድ አካባቢውን ምቹ ለማድረግ የውጭ ምንዛሬ መመሪያውን ማሻሻሉን ግንቦት 17 ቀን 2018 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
በአዲሱ ማሻሻያ መሠረት የንግድ ባንኮች የውጭ ምንዛሬ አካውንት እና የውጭ ምንዛሬ ተመላሽ ሂሳብ አካውንት ላላቸው ተቋማት የብሔራዊ ባንክን ቅድመ ፈቃድ ሳይጠብቁ የብድር ማረጋገጫ ሰነድ እና የሰነድ መክፈያ ማጽደቅ ይችላሉ ተብሏል፡፡
በገቢና ወጪ ንግድ ላይ የተሰማሩ ተቋማትም የባንኮችን ቅድመ ፈቃድ ሳይጠብቁ በሰነድ መክፈያ አሠራር አማካኝነት ዕቃዎችን ማዘዝና ማጓጓዝ እንደሚችሉ በአዲሱ መመሪያ ተደንግጓል።
በተጨማሪም ብሔራዊ ባንኩ ከዓለም አቀፍ አሠራር ጋር ለማስማማት በባንኮች የሚጠየቁ የውጭ ምንዛሬ ፈቃድ አገልግሎት ክፍያዎችን በዓመታዊ ስሌት እና እንደ ሰነዱ የአገልግሎት ዘመን ተመጣጣኝ ሆኖ እንዲሰላ ተወስኗል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X