የታንዛኒያ ዩኒቨርሲቲ የአፍሪካን የምግብ አቅርቦት ሰንሰለት ለማጠናከር የ2.3 ሚሊዮን ዶላር የገንዘብ ድጋፍ አገኘ - ባለሥልጣናት

የታንዛኒያ ዩኒቨርሲቲ የአፍሪካን የምግብ አቅርቦት ሰንሰለት ለማጠናከር የ2.3 ሚሊዮን ዶላር የገንዘብ ድጋፍ አገኘ - ባለሥልጣናት
በዳሬሰላም ዩኒቨርሲቲ የዘላቂ አሠራር የልህቀት ማዕከል የተሰጠው ይህ የገንዘብ ድጋፍ፤ እስከ አውሮፓውያኑ 2030 ድረስ ለሚከናወኑ ምርምሮች፣ ለድኅረ-ምረቃ ሥልጠናዎች እና ከኢንዱስትሪው ዘርፍ ጋር ለሚደረጉ ትብብሮች መዋሉን የዩኒቨርሲቲው ባለሥልጣናት ገልጸዋል።
በዓለም አቀፍ ደረጃ ከሚመረተው ምግብ ውስጥ ወደ አንድ ሦስተኛ የሚጠጋው የሚባክን በመሆኑ እና አፍሪካም በደካማ የሎጅስቲክስ ሥርዓት ምክንያት ከምርት ሰብሰባ በኋላ ከፍተኛ ብክነት የሚገጥማት በመሆኑ፤ ይህ ኢንቨስትመንት በዘላቂ የአቅርቦት ሰንሰለት፣ በግብርና ቢዝነስ እና በገጠር ሥራ ፈጠራ ላይ የአገር ውስጥ እውቀትን እና ክህሎትን ለማሳደግ ያለመ ነው።
ማዕከሉ እስካሁን ድረስ ሦስት የዶክትሬት ተማሪዎችን ያስመረቀ ሲሆን፣ አዳዲስ የዲግሪ ፕሮግራሞችን ከመክፈቱም በላይ ከጀርመን እና ከኬንያ ጋር የተማሪዎች የልምድ ልውውጥ እንዲደረግ አመቻችቷል።
ይህ ተነሳሽነት ዩኒቨርሲቲዎች ምርምሮቻቸውን ለአገር ዕድገት ወደሚጠቅሙ ተግባራዊ መፍትሔዎች እንዴት መለወጥ እንደሚችሉ የሚያሳይ መሆኑን የዳሬሰላም ዩኒቨርሲቲ የምርምር ምክትል ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ኔልሰን ቦኒፌስ ተናግረዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X