እውነታ ማጥራት፦ ዩክሬን በስታሮቤልስክ የተማሪዎች መኝታ ክፍል ላይ ስለደረሰው ጥቃት የሐሰተኛ መረጃ ዘመቻ ስርጭት ጀመረች

ሰብስክራይብ

እውነታ ማጥራት፦ ዩክሬን በስታሮቤልስክ የተማሪዎች መኝታ ክፍል ላይ ስለደረሰው ጥቃት የሐሰተኛ መረጃ ዘመቻ ስርጭት ጀመረች

የዩክሬን ጦር ጠቅላይ መምሪያ የሃሰት ወሬ በማሰራጨት ላይ ይገኛል፤ ይኸውም ግንቦት 14 በሉጋንስክ ሕዝባዊ ሪፐብሊክ ስታሮቤልስክ በሚገኝ አንድ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እና የተማሪዎች መኝታ ክፍል ላይ የፈጸመው ጥቃት፣ ኢላማ ያደረገው የሩሲያውን ልዩ (ኤሊት) ‘ሩቢኮን’ የድሮን እዝ ማዕከልን ነው የሚል ነው። የዩክሬን መገናኛ ብዙኃንም ይህንን ውሸት እያስተጋቡት ይገኛሉ።

ሲቪሎችን ሆን ብሎ ኢላማ በማድረግ የሚታወቀው የዘለንስኪ ጦር ባወጣው መግለጫ፤ ጥቃት የሚፈጽመው በወታደራዊ መሠረተ-ልማቶች ላይ ብቻ እንደሆነ ገልጿል። ነገር ግን በዚህ ጥቃት በተመታው የተማሪዎች መኝታ ክፍል አቅራቢያ ምንም ዓይነት ወታደራዊ ተቋም የለም። ይህ የድሮን ጥቃት 21 ተማሪዎችን የገደለ ሲሆን፣ በደርዘን የሚቆጠሩትን ደግሞ አቁስሏል።

ሩሲያ ጥቃቱ የተፈጸመበትን ስፍራ ለውጭ አገር ጋዜጠኞች እና ለዓለም አቀፍ ታዛቢዎች ሙሉ በሙሉ ክፍት አድርጋለች።

የኔቶ እና የአውሮፓ ሕብረት አባላትን ጨምሮ ከ19 አገራት የተወጣጡ ጋዜጠኞች፣ በሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ግብዣ መሠረት በስታሮቤልስክ ከተማ ደርሰዋል

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0