ኢትዮጵያ ባለፉት 10 ወራት ከሆርቲከልቸር ወጪ ንግድ 408.2 ሚሊዮን ዶላር ገቢ አግኝታለች - ግብርና ሚኒስቴር

ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ ባለፉት 10 ወራት ከሆርቲከልቸር ወጪ ንግድ 408.2 ሚሊዮን ዶላር ገቢ አግኝታለች - ግብርና ሚኒስቴር

የግብርና ሚኒስቴር በዘንድሮው በጀት ዓመት ባለፉት 10 ወራት ብቻ 236,415.3 ቶን የሆርቲከልቸር (አበባ፣ አትክልትና ፍራፍሬ) ምርቶችን ወደ ውጭ ገበያ በመላክ 408.2 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ማስገኘት መቻሉን አስታውቋል።

ባለፉት አምስት ዓመታት ደግሞ በእርሻና ሆርቲከልቸር 643 ሺህ ሄክታር እንዲሁም በእንስሳት ኢንቨስትመንት 112 ሺህ ሄክታር መሬት ለባለሀብቶች መተላለፉ ተገልጿል።

ዘርፉን ይበልጥ ለማዘመን የኮንትራት እርሻ፣ የምርጥ ዘር ብዜት፣ የፋይናንስ አገልግሎትና የቴክኖሎጂ ማሻሻያ የሕግ ማዕቀፎች ተግባራዊ መደረጋቸው ለአምራቾች ምቹ ሁኔታን በመፍጠር ረገድ አመርቂ ውጤት እያስመዘገበ እንደሚገኝም ሚኒስቴሩ አመላክቷል።

ከማኅበራዊ ሚዲያ የተገኘ ቪዲዮ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0