አሜሪካ እና ኢራን የሆርሙዝ ወሽመጥን ክፍት የሚያደርግ የ60 ቀናት የመግባቢያ ስምምነት ሊፈራረሙ ይችላሉ - ዘገባ
15:13 24.05.2026 (የተሻሻለ: 15:14 24.05.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
አሜሪካ እና ኢራን የሆርሙዝ ወሽመጥን ክፍት የሚያደርግ የ60 ቀናት የመግባቢያ ስምምነት ሊፈራረሙ ይችላሉ - ዘገባ
አክሲዮስ የአሜሪካ ባለሥልጣንን ጠቅሶ እንደዘገበው፤ የመግባቢያ ስምምነቱ የሆርሙዝ ወሽመጥ ያለ ምንም የክፍያ ታሪፍ በድጋሚ ክፍት እንዲሆን የሚያደርግ ሲሆን፣ በምላሹም አሜሪካ በኢራን ወደቦች ላይ የጣለችውን እገዳ ታነሳለች እንዲሁም ለነዳጅ ሽያጭ የተጣሉ ማዕቀቦች እንዲላሉ (ፈቃድ እንዲያገኙ) ታደርጋለች።
▫ የኒውክሌር ጉዳዮች ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷቸዋል፤ ኢራን የኒውክሌር መሣሪያዎችን ፈጽሞ ላለማልማት እና የዩራኒየም ማበልጸግ ሥራን ማቆምን በተመለከተ ለመደራደር የቃል ቁርጠኝነት የሰጠች ቢሆንም፣ እስካሁን ግን ምንም የጸና (የተረጋገጠ) ነገር የለም።
▫ የአሜሪካ ጦር ለሙሉ 60 ቀናት በቀጣናው ይቆያል፤ ጦሩ የሚወጣው የመጨረሻ ስምምነት ላይ ከተደረሰ ብቻ ይሆናል።
▫ የሊባኖስ የተኩስ አቁም ስምምነት ተካቷል፤ ኔታንያሁ ቅዳሜ ዕለት ከትራምፕ ጋር ባደረጉት የስልክ ውይይት በዚህ ቅድመ-ሁኔታ ላይ ስጋታቸውን መግለጻቸውን አንድ የእስራኤል ባለሥልጣን አረጋግጠዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X