ኢትዮጵያዊው አትሌት መሐመድ ኢሳ በኬፕታውን ማራቶን የውድድሩን ክብረወሰን በመስበር አሸነፈ
14:33 24.05.2026 (የተሻሻለ: 14:34 24.05.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያዊው አትሌት መሐመድ ኢሳ በኬፕታውን ማራቶን የውድድሩን ክብረወሰን በመስበር አሸነፈ
በደቡብ አፍሪካ በተካሄደው የኬፕታውን ማራቶን ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሁለቱም ፆታ የበላይነቱን ወስደው አሸንፈዋል።
በወንዶች አትሌት መሐመድ ኢሳ 2፡04፡55 በሆነ ሰዓት በመግባት ውድድሩን በቀዳሚነት ከማጠናቀቅ ባለፈ በአፍሪካ ምድር የተመዘገበ ፈጣኑን የማራቶን ሰዓት የግሉ ማድረግ ችሏል።
ሌላኛው ኢትዮጵያዊ አትሌት ይሁንልኝ አዳነ 2፡04፡59 በሆነ ሰዓት ሁለተኛ በመግባት የግል ምርጥ ሰዓቱን አስመዝግቧል።
በዚሁ ውድድር የተሳተፈው ታዋቂው የኬንያ አትሌት ኤሉድ ኪፕቾጌ ውድድሩን በ16ኛ ደረጃ አጠናቋል።
በሴቶች ማራቶን፦
አትሌት ደራ ዲዳ 2፡23፡18 በሆነ ሰዓት ቀዳሚ ሆናለች።
አትሌት መክተዉት ፍቅር ሁለተኛ
አትሌት ዋጋነሽ መካሻ ሦስተኛ በመሆን አጠናቃለች።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X