ሩሲያ የ2011ዱ የሊቢያ ተቃውሞ ክስ ከዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት እንዲነሳ ለተመድ ጥሪ ማቅረቧን በተመድ የሩሲያ ምክትል መልዕክተኛ አስታወቁ

ሰብስክራይብ

ሩሲያ የ2011ዱ የሊቢያ ተቃውሞ ክስ ከዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት እንዲነሳ ለተመድ ጥሪ ማቅረቧን በተመድ የሩሲያ ምክትል መልዕክተኛ አስታወቁ

​የሊቢያ ባለሥልጣናት እ.ኤ.አ 2011 በሀገሪቱ የተነሳውን ተቃውሞ በኃይል አፍነዋል በሚል በዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት ምርመራ ቢከፈትም፤ ዋና ተጠርጣሪዎች ሙአማር ጋዳፊ እና ልጃቸው ሰይፍ አል-ኢስላም በቁጥጥር ስር ከመዋላቸው በፊት እንደተገደሉ እና ሌላኛው ተጠርጣሪ ከክሱ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት እንደሌላቸው ማሪያ ዛቦሎትስካያ ገልጸዋል።

​የጋዳፊ እና የልጃቸውን ሞት ተከትሎ ጉዳዩ ተጠርጣሪዎች ባለመኖራቸው መዘጋት ሲገባው በእስር ቤቶች ውስጥ የተፈጸሙ ወንጀሎችን ለመመርመር እንደገና እንዲዋቀር መደረጉን አስታውሰዋል።

​ይህ በእንዲህ እንዳለ ፍርድ ቤቱ በሰብዓዊነት ላይ በተፈጸሙ ወንጀሎች የተጠረጠሩ የአውሮፓ አካላትን ተጠያቂ ለማድረግ ፍላጎት እንደሌለው ዛቦሎትስካያ አጽንኦት ሰጥተዋል።

"እነርሱ የፍርድ ቤቱ ደጓሚዎች ናቸው፤ ደጓሚዎች ደግሞ አይከሰሱም" ሲሉ ዲፕሎማቷ ተናግረዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0