ኢትዮጵያ በዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት ድርድር ማዕቀፍ ከሕንድ ጋር የሁለትዮሽ የገበያ ዕድል ስምምነት ተፈራረመች
19:55 23.05.2026 (የተሻሻለ: 20:04 23.05.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ በዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት ድርድር ማዕቀፍ ከሕንድ ጋር የሁለትዮሽ የገበያ ዕድል ስምምነት ተፈራረመች
ስምምነቱ ኢትዮጵያ ወደ ዓለም አቀፉ የባለብዙ ወገን የንግድ ሥርዓት ለመቀላቀል ለምታደርገው ጉዞ ትልቅ ታሪካዊ ምዕራፍ ነው ተብሏል።
ሰነዱን በጄኔቫ የተመድ እና ሌሎች ዓለም አቀፍ ድርጅቶች የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ፀጋአብ ከበበው እና በዓለም ንግድ ድርጅት የሕንድ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ሴንቲል ፓንዲያን ፈርመውታል።
ስምምነቱ በሸቀጦችና በአገልግሎት ዘርፎች ላይ በጋራ የተደረሱ የገበያ ተደራሽነት ግዴታዎችንና ጥቅሞችን ያካተተ እንደሆነ በጄኔቫ የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ ጽሕፈት ቤት አስታወቋል።
"ሕንድ አስተማማኝና የረጅም ጊዜ የልማት አጋር ናት" ሲሉ አምባሳደር ፀጋአብ ፊርማውን ተከትሎ ተናግርዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X