ዚምባብዌ ከቻይና የዜሮ-ታሪፍ ዕድል ተጠቃሚ ለመሆን የንጽህና እና የዕፅዋት ጤና ጥበቃ ደረጃዎችን ማሟላት አለባት - የንግድ ኮሚሽን
17:45 23.05.2026 (የተሻሻለ: 17:54 23.05.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ዚምባብዌ ከቻይና የዜሮ-ታሪፍ ዕድል ተጠቃሚ ለመሆን የንጽህና እና የዕፅዋት ጤና ጥበቃ ደረጃዎችን ማሟላት አለባት - የንግድ ኮሚሽን
ቻይና ለአፍሪካ የወጪ ንግድ ምርቶች የፈቀደችውን ከቀረጥ ነፃ ዕድል ሙሉ በሙሉ ለመጠቀም ዚምባብዌ የንጽህና እና የዕፅዋት ጤና ጥበቃ "ኤስፒኤስ" መስፈርቶችን የማሟላት አቅሟን ማጠናከር እንዳለባት የሀገሪቱ የውድድር እና የታሪፍ ኮሚሽን ገልጿል።
የአትክልትና ፍራፍሬ ልማት በሁለቱ ሀገራት የሁለትዮሽ ንግድ ስልታዊ ዘርፍ እየሆነ መምጣቱን የጠቀሰው ኮሚሽኑ፤ ነገር ግን የ "ኤስፒኤስ" መስፈርቶች ለታዳጊ ሀገራት ቴክኒካዊ ዘብ ሆነው እንደሚያገለግሉ አመልክቷል።
ለዚምባብዌ እነዚህን ደረጃዎች ማሟላት ከታሪፍ ዕድሎች እኩል ወሳኝ መሆኑን ኮሚሽኑ አፅንዖት ሰጥቶታል።
"የኤስፒኤስ" ፕሮቶኮሎችን ከእገዳነት ወደ አጋዥነት ለመቀየር እና የዚምባብዌ ምርቶች በቻይና ገበያ ተወዳዳሪና እምነት የሚጣልባቸው ሆነው እንዲቀጥሉ ለማድረግ፤ የደረጃ ማሟያ ሥርዓቶች ላይ ኢንቨስት እንዲደረግ እና አሳታፊ የዕሴት ሰንሰለቶች እንዲዘረጉ ጥሪ አቅርቧል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X