አፍሪካ ሙስናን ለመዋጋትና ራስን የመቻል አቅሟን ለመገንባት ጠንካራ ውስጣዊ ኦዲት ዋነኛ መሣሪያዋ ነው - የአፍሪካ ውስጣዊ ኦዲት ማኅበራት ፌዴሬሽን ኃላፊ
14:43 23.05.2026 (የተሻሻለ: 14:44 23.05.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
አፍሪካ ሙስናን ለመዋጋትና ራስን የመቻል አቅሟን ለመገንባት ጠንካራ ውስጣዊ ኦዲት ዋነኛ መሣሪያዋ ነው - የአፍሪካ ውስጣዊ ኦዲት ማኅበራት ፌዴሬሽን ኃላፊ
የአፍሪካ ውስጣዊ ኦዲት ሙያ ተቋማትን ማጠናከር እና መንግሥታት የልማት ግቦቻቸውን እንዲያሳኩ ማገዝ እንዳለበት፤ የአፍሪካ ውስጣዊ ኦዲት ማኅበራት ፌዴሬሽን የደቡብዊ አፍሪካ ቀጣናዊ ምክትል ሊቀመንበር ታፊሬይ ኒያማዛና ገልጸዋል።
በኬፕ ታውን ከግንቦት 16 እስከ 21 ከሚካሄደው የፌዴሬሽኑ የአስተዳደር መድረክ ቀደም ብለው ሃሳባቸውን ያከፈሉት ኃላፊው፤ ጠንካራ የኦዲት አሠራሮች ማጭበርበር እና ሙስናን ለመግታት ከመርዳት በላይ እንደ የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ያሉ አኅጉራዊ ተነሳሽነቶች ስኬታማ እንዲሆኑ ምቹ ሁኔታዎችን ይፈጥራሉ ብለዋል።
"ተጠያቂነት በሁሉም ላይ እኩል የሚሠራበት እና የሥነ-ምግባር መርሆዎች ዕለታዊ ውሳኔዎችን የሚመሩበት ባሕል እንዲሰርጽ"ለስፑትኒክ አፍሪካ በሰጡት አስተያየት አሳስበዋል።
ℹ “አንድ ፌዴሬሽን፣ አንድ አፍሪካ፣ አንድ ድምፅ” በሚል መሪ ቃል የሚካሄደው ይህ መድረክ፤ በአኀጉሪቱ የሙያውን ዘርፍ የወደፊት ዕጣ ፈንታ ለመቅረጽ የፖሊሲ አውጭዎችን፣ የንግድ መሪዎችን እና ባለሙያዎችን አንድ ላይ ያሰባስባል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X