ፒያሳ የቱሪስት ስበትን በጨመሩ መሠረተ ልማቶች ታሪካዊ ቦታ ሆኗል - የአዲስ አበባ ከንቲባ
14:15 23.05.2026 (የተሻሻለ: 14:24 23.05.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ፒያሳ የቱሪስት ስበትን በጨመሩ መሠረተ ልማቶች ታሪካዊ ቦታ ሆኗል - የአዲስ አበባ ከንቲባ
የመዲናዋ ከንቲባ “ዶሮ ማነቂያ” አከባቢ የተሠራውን ዘመናዊ የንግድ እና የትራንስፖርት ተርሚናል አስመርቀዋል፡፡
በዓድዋ የንግድ እና የትራንስፖርት ሁለገብ ማዕከል የተካተቱ አገልግሎቶች፦
ከ101 በላይ ዘመናዊ የንግድ ሱቆች፣
ባለ ሁለት ወለል የምድር ውስጥ መኪና ማቆሚያ፣
የተደራጁ የታክሲና የባስ ተርሚናሎች፣
ደረጃቸውን የጠበቁ ካፌና ምግብ ቤቶች፣
የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች መሙያ ጣቢያዎች።
“ፒያሳ ኣካባቢ የኮሪደር ልማት የጀመርንበት ነው። ዛሬ ፒያሳ የጋራ ታሪካችንን የዓድዋ ድል መታሰቢያን የገነባንበት እና የሀገራት መሪዎች ለጀግኖች ሰማዕቶቻችን የአበባ ጉንጉን የሚያኖሩበትን ጨምሮ በርካታ የጋራ መገልገያ እና የቱሪስት ስበትን የጨመሩ መሰረተ ልማቶች የሠራንበት ታሪካዊ ቦታ ሆኗል” ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናግረዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X