በኤም23 እና በኮንጎ ጦር መካከል ያለው ግጭት የኢቦላ ወረርሽኝ ምላሽን አስተጓጉሏል - ዚምባብዌያዊ ጋዜጠኛ

ሰብስክራይብ

በኤም23 እና በኮንጎ ጦር መካከል ያለው ግጭት የኢቦላ ወረርሽኝ ምላሽን አስተጓጉሏል - ዚምባብዌያዊ ጋዜጠኛ

​ግጭት ባለባቸው አካባቢዎች ስለ ሕዝብ ጤና ሁኔታ ወቅታዊ መረጃዎችን በወቅቱ ማግኘት ላይ አዳጋች ሊሆን እንደሚችል የጤና ተሟጋች እና "የሄልዝ ታይምስ" ዋና አዘጋጅ ማይክል ግዋሪሳ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

​በተጨማሪም፤ ኢቦላን "የነጭ ሰው በሽታ" በማለት የሚነዙ ወሬዎችን የመሰሉ የተሳሳቱ መረጃዎች የህክምና ማዕከል ማቃጠልን ጨምሮ ጥቃቶችን በማነሳሳት ለወረርሽኙ ምላሽ ለመስጠት የሚደርጉ ጥረቶችን ይበልጥ እንዳስተጓጎሉ ገልጸዋል።

ሆኖም የዓለም ጤና ድርጅት እና የአፍሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማዕከል ወረርሽኙን ለመከላከል የፋይናንስ እና የሰው ኃይል እያሰባሰቡ በመሆኑ፤ ኢቦላ በመላው አፍሪካ አሁንም ከፍተኛ ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ ሆኖ ቀጥሏል ሲሉ ጋዜጠኛው አፅንዖት ሰጥተዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0