የቡና ምርት በአምስት ዓመት ግዜ ውስጥ የሦስት ዕጥፍ ጭማሪ አሳይቷል - የኢትዮጵያ ቡና እና ሻይ ባለሥልጣን
09:30 23.05.2026 (የተሻሻለ: 09:34 23.05.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የቡና ምርት በአምስት ዓመት ግዜ ውስጥ የሦስት ዕጥፍ ጭማሪ አሳይቷል - የኢትዮጵያ ቡና እና ሻይ ባለሥልጣን
የኢትዮጵያ ቡና ምርት ባለፉት ጥቂት ዓመታት በተከናወኑ የለውጥ ሥራዎች ከፍተኛ ዕድገት እያስመዘገበ እንደሚገኝ የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አዱኛ ደበላ ለስፑትኒክ አፍሪካ ገልጸዋል።
"ላለፉት አራት አምስት ዓመታት በየዓመቱ የምናመርተው የምርት መጠን እጅግ በጣም እየጨመረ ነው። የዛሬ አምስት ዓመት አጠቃላይ ምርታችን 500 ሺህ ሜትሪክ ቶን ነበር፤ ዛሬ ላይ ግን በሀገር ደረጃ ከ1.5 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን በላይ እያመረትን ነው።"
ይህ ዕድገት የተገኘው በሦስት ወሳኝ እርምጃዎች እንደሆነ ጠቅሰዋል፦
ያረጁ ቡናዎችን ቆርጦ በማንሳት ሥራ፣
የፓኬጅ ለውጥ፣
የአረንጓዴ አሻራ መርኃ-ግብር የቡና ተከላ።
የአሜሪካ የግብርና መምሪያ ኢትዮጵያ ኢንዶኔዢያን በመቅደም በዓለም አራተኛዋ ግዙፍ ቡና አምራች ትሆናለች ማለቱን አስመልክቶ በሰጡት አስተያየት፤ "እስካሁን ወደ 5.6 ሚሊዮን ከረጢት ኤክስፖርት አድርገናል" ሲሉ ተናግረዋል። ሪፖርቱ የኢትዮጵያን ‘ስፔሻሊቲ አረቢካ’ ቡና ብቻ የለየ ሊሆን እንደሚችልም አንስተዋል።
"የእኛ የስፔሻሊቲ አረቢካ ፐርሰንቴጅ ሲሰላ 40% አካባቢ ነው። ስለዚህ እነሱ 11.9 ሚሊዮን አካባቢ ያስቀመጡት ትንበያ የእኛን የስፔሻሊቲ ቡና ፐርሰንቴጅ ብቻ ነው የሚሸፍነው። እኛ ከ60% በላይ የምናመርተውና ‘ኮሜርሻል’ የሚባለው ቡና በዚህ ውስጥ ስላልተካተተ ነው እንጂ ከቬትናም ቀጥለን ሦስተኛ ትልቅ ቡና አምራች ሀገር ነን። ኮሎምቢያንና ኢንዶኔዥያንማ ቀድመን ባለፈው ዓመት በልጠናቸዋል።"
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X