ኢትዮጵያ ኢንዶኔዢያን በመቅደም በዓለም አራተኛዋ ግዙፍ ቡና አምራች ልትሆን ነው

ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ ኢንዶኔዢያን በመቅደም በዓለም አራተኛዋ ግዙፍ ቡና አምራች ልትሆን ነው

በአሜሪካ የግብርና መምሪያ የቅርብ ጊዜ ዓመታዊ የቡና ሪፖርት መሠረት፤ በ2026/27 የኢትዮጵያ የቡና ምርት 726 ሺህ ቶን ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል። በአንጻሩ የኢንዶኔዢያ ምርት 682 ሺህ 800 ቶን እንደሚሆን ተተንብይዋል።

ትንበያው እውን ከሆነ ኢትዮጵያ ባለፉት አምስት ዓመታት ውስጥ በጠቅላላ የቡና ምርት ለሦስተኛ ጊዜ ኢንዶኔዢያን (ከ2023/24 እና 2024/25 የምርት ዘመናት በመቀጠል) ትበልጣለች።

ይህ ከፍተኛ ጭማሪ ኢትዮጵያ በተከታታይ ዓመታት የቡና ምርት ዕድገት የምታስመዘግብበት ይሆናል

በ2024/25፣ 687 ሺህ 600 ቶን፣

በ2025/26 693 ሺህ 600 ቶን፣

ምቹ የአየር ንብረት ሁኔታዎች፣ በመንግሥት የሚደገፉ የመሬት ማገገም ፕሮግራሞች፣ እየጨመረ የመጣው የግሉ ዘርፍ ኢንቨስትመንት እና ግብርናን የማዘመን ሥራዎች የምርት ዕድገቱ አቀጣጣይ እንደሆኑ ተገልጿል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0