ዩክሬን በሩሲያ ሉሃንስክ ሕዝባዊ ሪፐብሊክ ኮሌጅ ላይ የሰነዘረችው ጥቃት የኪየቭ አገዛዝን አሸባሪነት ያረጋግጣል - ፑቲን
ዩክሬን በሩሲያ ሉሃንስክ ሕዝባዊ ሪፐብሊክ ኮሌጅ ላይ የሰነዘረችው ጥቃት የኪየቭ አገዛዝን አሸባሪነት ያረጋግጣል - ፑቲን
የሩሲያ ፕሬዚዳንት የዩክሬን ጦር ኃይል ከኪየቭ ሕገ-ወጥ፣ ሙሰኛ ጁንታ የሚሰጡትን የወንጀል ትዕዛዞች ውድቅ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ፑቲን በመግለጫቸው ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች፦
በሩሲያዋ የሉሃንስክ ሕዝባዊ ሪፐብሊክ በሚገኝ አንድ ኮሌጅ ላይ ዩክሬን ባደረሰችው የድሮን ጥቃት የሞቱ ሰዎች ቁጥር ወደ ስድስት ከፍ ብሏል።
የዩክሬን ጦር ኃይሎች ሉሃንስክ ውስጥ በሚገኝ የተማሪዎች ዶርም ላይ የሰነዘሩት ጥቃት በአጋጣሚ የተፈጠረ አይደለም። ጥቃቱ የተፈጸመው በሦስት ዙር ሲሆን በአቅራቢያው ምንም ዓይነት ወታደራዊ ተቋማት የሉም።
በመኝታ ክፍሉ ላይ የተፈጸመው ጥቃት ሩሲያ ከማን ጋር እየተጋፈጠች እንደሆነ ያሳየ ነው።
በግንባር ላይ ያለው ሁኔታ ለዩክሬን የጦር ኃይሎች ከከባድ ወደ አስከፊ እየተቀየረ ነው፡፡ ምዕራባውያን የሚሰጡት ዕርዳታም ሆነ በኃይል የሚደረገው የውትድርና ምልመላ ሊረዳቸው አልቻለም።
በዩክሬን ጦር ውስጥ የሚታየው የወታደሮች ኩብለላ አስከፊ ደረጃ ላይ ደርሷል።
ፑቲን በሩሲያ ስታሮቤልስክ በሚገኝ አንድ ኮሌጅ ላይ በደረሰው የዩክሬን ጥቃት ለተገደሉ ሰዎች የአንድ ደቂቃ የህሊና ጸሎት አድርገዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X