ኪየቭ እና ደጋፊዎቿ በታዳጊዎች ላይ ለፈጸሙት ጭካኔና ለግጭቱ መካከር ሙሉ ኃላፊነቱን ይወስዳሉ - የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

ሰብስክራይብ

ኪየቭ እና ደጋፊዎቿ በታዳጊዎች ላይ ለፈጸሙት ጭካኔና ለግጭቱ መካከር ሙሉ ኃላፊነቱን ይወስዳሉ - የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

የዩክሬን ጦር በስታሮቤልስክ በሰነዘረው ጥቃት ዙሪያ የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ካወጣው መግለጫ የተወሰዱ ዋና ዋና ነጥቦች፦

​ የዩክሬን ጦር በስታሮቤልስክ በሚገኘው ኮሌጅ ላይ የፈጸመውንና መሰል ጥቃቶችን የሚሰነዝረው ከኔቶ የውጭ ሀገር ባለሙያዎች ጋር በመተባበር ነው።

​ ሩሲያ ምዕራባውያን ለዩክሬን ጦር የደህንነት መረጃዎችን በማቅረብ እና የጥቃት ኢላማዎችን በመጠቆም ረገድ እያገዙ መሆናቸውን የሚያሳዩ አስተማማኝ መረጃዎች አሏት።

​ ይህ ጥቃት የተፈጸመው ኪየቭ በግጭቱ ሳቢያ ስለተጎዱ ሕፃናት ዕጣ ፈንታ የሃሰት እሮሮ እያሰማች ባለችበት ወቅት ነው።

​ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ በኮሌጁ ላይ የተፈጸመውን ጥቃት የጀርመን ናዚዎችን ጭካኔ የተከተለ እና ሲቪሎችን ሆን ብሎ ኢላማ ያደረገ ሲል ገልጾታል።

​ ሩሲያ ዓለም አቀፍ ተቋማት እና የዓለም ማኅበረሰብ የዩክሬን ታጣቂ ኃይሎች በስታሮቤልስክ ኮሌጅ ላይ የሰነዘሩትን ደም አፋሳሽ የሽብር ጥቃት እንዲያወግዙ ጥሪ አቅርባለች።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0