በጀጎል የዓለም ቅርስ ግንብ ውስጥ የተከናወነው የኮሪደር ልማት የቱሪስቶችን ፍሰት እንዳሳደገ ተገለጸ
14:40 22.05.2026 (የተሻሻለ: 14:44 22.05.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
በጀጎል የዓለም ቅርስ ግንብ ውስጥ የተከናወነው የኮሪደር ልማት የቱሪስቶችን ፍሰት እንዳሳደገ ተገለጸ
በከተማዋ ጥንታዊ ግንብ ውስጥ ከ22 ኪ.ሜ በላይ የኮሪደር ልማት እንዲሁም 3.4 ኪ.ሜ የሚሸፍን የጀጎል ግንብ ዙሪያ መልሶ ማልማትና የአረንጓዴ ሥፍራ ሥራ መከናወኑንና ቢሮ የሀረሪ ክልል ባሕል፣ ቅርስና ቱሪዝም ቢሮ አስታውቋል።
በልማቱ ሺህ ዘመናትን ያስቆጠሩ ታሪካዊና ጥንታዊ ቅርሶችን ለጎብኚዎች ምቹና ማራኪ ለማድረግ ውጤታማ ሥራዎች እንደተከናወኑም ቢሮው በማሳያነት ጠቅሷል።
“አካባቢያዊ ሀብትና እውቀት በመጠቀም የተከናወኑ ሥራዎች የቅርሱን ይዘትና ታሪካዊነት ውብ አድርገውታል” ሲሉ የቢሮው ኃላፊ አሚር ረመዳን ገልጸዋል።
በዚህም ከፍተኛ ቁጥር የሀገር ውስጥ እና የውጭ ሀገር ጎብኚዎችን መሳብ እንደተቻለ እና ከሰባት ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል መፈጠሩ ተገልጿል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X