ኬንያ የነዳጅ ዋጋ ንረትን ተከትሎ የተቀሰቀሰውን ውጥረት ለማርገብ በናፍጣ ዋጋ ላይ ቅናሽ አደረገች

ሰብስክራይብ

ኬንያ የነዳጅ ዋጋ ንረትን ተከትሎ የተቀሰቀሰውን ውጥረት ለማርገብ በናፍጣ ዋጋ ላይ ቅናሽ አደረገች

​ ከከፍተኛ የነዳጅ ዋጋ መጨመር ጋር በተያያዘ የተቀሰቀሰውንና ለሰው ሕይወት መጥፋት ምክንያት የሆነውን ተቃውሞ እንዲሁም ለሁለት ቀናት የተደረገውን የሕዝብ ትራንስፖርት የሥራ ማቆም አድማ ተከትሎ በሸማቾች ላይ የሚደርሰውን ጫና ለመቀነስ መንግሥት የናፍጣ ዋጋን እንደሚቀንስ ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ በዛሬው ዕለት አስታውቀዋል።

​በሰኔ-ሐምሌ የዋጋ ክለሳ ዑደት የማደያ ዋጋን ለማረጋጋት የናፍጣ ዋጋ በ0.07 ዶላር እንደሚቀንስ የገለጹት ሩቶ፤ መንግሥት ከሚያዚያ እስከ ሰኔ ባለው ጊዜ ውስጥ ለነዳጅ ዋጋ ድጎማ ቢያንስ 216.6 ሚሊዮን ዶላር ወጪ ማድረጉንም አክለዋል።

​ ውሳኔው ዓለም አቀፉን የነዳጅ አቅርቦት እጥረት እና ከመካከለኛው ምስራቅ ግጭት ጋር ተያያዞ በተፈጠረው የኃይል አቅርቦት ወጪ መናር ምክንያት የነዳጅ ዋጋ እስከ 23.5 በመቶ የሚደርስ ከፍተኛ ጭማሪ ማሳየቱን ተከትሎ የመጣ ነው።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0