የሩሲያ እና ቤላሩስ የኒውክሌር ጦር ኃይሎች የጋራ ልምምድ ሁለተኛው ምዕራፍ ቪዲዮ በሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር ይፋ ተደረገ
17:35 21.05.2026 (የተሻሻለ: 17:44 21.05.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የሩሲያ እና ቤላሩስ የኒውክሌር ጦር ኃይሎች የጋራ ልምምድ ሁለተኛው ምዕራፍ ቪዲዮ በሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር ይፋ ተደረገ
በልምምዱ አኅጉር አቋራጭ፣ ሃይፐርሶኒክ እና ከአየር የሚተኮሱ የክሩዝ ሚሳኤሎች መወንጨፋቸውን ሚኒስቴሩ አስታውቋል።
ከሚኒስቴሩ መግለጫ የተገኙ አንኳር ነጥቦች፦
🟠 የኒውክሌር ሰርጓጅ መርከብ አባላት ከጥልቅ ስፍራ "ሲኔቫ" የተሰኘ አኅጉር አቋራጭ ባሊስቲክ ሚሳኤል ተኩሰዋል፣
🟠 የ "ያርስ" አኅጉር አቋራጭ ባሊስቲክ ሚሳኤል ከፕሌሴትስክ የጠፈር ማዕከል ተተኩሶ በሩሲያ ካምቻትካ ክልል በሚገኝ የሙከራ ጣቢያ አርፏል፣
🟠 የቤላሩስ ጦር ሠራዊት አባላት ከካፑስቲን ያር የሙከራ ጣቢያ በ "ኢስካንደር-ኤም" የሚሳኤል ሥርዓት የባሊስቲክ ሚሳኤል የተግባር ተኩስ ልምምድ አድርገዋል፣
🟠 በሥልጠናው ላይ የተሳተፈው የ "ቱ-95ኤምኤስ" ጦር አውሮፕላን፤ ከአየር ላይ የሚተኮሱ ሃይፐርሶኒክ የክሩዝ ሚሳኤሎችን የተኮሰ ሲሆን "ሚግ-31ኤም" ተዋጊ ጄት ደግሞ "ኪንዛል" የተሰኘውን ሚሳኤል አስወንጭፏል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X