ኢትዮጵያ እና ደቡብ ሱዳን የቦማ-ጋምቤላ ድንበር ተሻጋሪ የዱር እንስሳት ጥበቃን ለማጠናከር ተስማሙ
17:22 21.05.2026 (የተሻሻለ: 17:24 21.05.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ እና ደቡብ ሱዳን የቦማ-ጋምቤላ ድንበር ተሻጋሪ የዱር እንስሳት ጥበቃን ለማጠናከር ተስማሙ
የሁለቱ ሀገራት የዱር እንሰሳት ጥበቃ ባለሥልጣን ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በድንበር ተሻጋሪ ፓርክ አስተዳደርና የኢትዮጵያ እና ደቡብ ሱዳን የጥበቃ ሥራ ትብብር ማጠናከርን በተመለከተ ምክክር አድርገዋል።
ስምምነቱ የኢትዮጵያ እና የደቡብ ሱዳን ድንበርን የሚያቋርጡ ወደ ስድስት ሚሊዮን የሚጠጉ የአጋዘን ዝርያዎችን ስደት በጋራ ማስተዳደር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ያተኮረ ነበር።
የቦማ-ጋምቤላ ድንበር ተሻጋሪ ጥበቃ ተነሳሽነት የቀጣናውን የብዝሃ ሕይወት ጥበቃ ያጠናክራል ተብሎ ይጠበቃል ሲል የኢትዮጵያ ዱር እንሰሳት ጥበቃ ባለሥልጣን አስታውቋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X