ኢትዮጵያ የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ በአየር ንብረት ለውጥ ዙሪያ ባካሄደው የድምጽ አሰጣጥ ላይ ተዐቅቦ አደረገች
15:45 21.05.2026 (የተሻሻለ: 15:54 21.05.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ በአየር ንብረት ለውጥ ዙሪያ ባካሄደው የድምጽ አሰጣጥ ላይ ተዐቅቦ አደረገች
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፖሊሲ ክንፍ፤ ሀገራት የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል እርምጃ የመውሰድ ሕጋዊ ግዴታ ይኖርባቸዋል የሚለውን የዓለም አቀፉን የፍትሕ ፍርድ ቤት ምክረ ሃሳብ አጽድቋል፡፡
በደሴቲቷ ሀገር ቫኑአቱ የቀረበው አስገዳጅ ያልሆነ የውሳኔ ሃሳብ፤ በ141 የድጋፍ ድምፅ፣ በ8 ተቃውሞ እና በ28 ተዐቅቦ ጸድቋል፡፡
ሩሲያ፣ ኢራን እና ዩናይትድ ስቴትስ የተቃውሞ ድምጽ ከሰጡ ሀገራት መካከል ሲሆኑ የ32ኛው የተመድ የአየር ንብረት ጉባኤ አስተናጋጇ ኢትዮጵያ ድምጽ ከመስጠት ተቆጥባለች፡፡
ሩሲያ እና ቻይና ቀደም ብለው ባወጡት የጋራ መግለጫ የአየር ንብረት ለውጥን ሰበብ በማድረግ፤ በታዳጊ ሀገራት ላይ የሚፈጸሙ አድሎዎችን እንደሚቃወሙ ገልጸዋል።
“...የአንድ ወገን ክልከላዎች የአየር ንብረት ለውጥ እርምጃዎችን እና በዓለም አቀፍ ደረጃ በተለይም በማደግ ላይ ባሉ ሀገራት ፍትሐዊ የኃይል ሽግግርን ያደናቅፋሉ፡፡”
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

© telegram sputnik_ethiopia