የአንድ ዋልታ ዓለም ሥርዓት ለበርካታ ውጥረቶች መነሻ ነው - ኒጀራዊ ባለሙያ
14:30 21.05.2026 (የተሻሻለ: 14:34 21.05.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የአንድ ዋልታ ዓለም ሥርዓት ለበርካታ ውጥረቶች መነሻ ነው - ኒጀራዊ ባለሙያ
እ.ኤ.አ በ1989 የሶቪየት ጎራ መፍረስን ተከትሎ የመጣው የነጠላ-ዋልታ ሥርዓት በመላው ዓለም ለተከሰቱ በርካታ ግጭቶች መነሻ መሆኑን የምዕራብ አፍሪካ ሕዝቦች ድርጅት አስተባባሪ ምክር ቤት አባል አላሳን አቡባከር ለስፑትኒክ አፍሪካ ገልጸዋል።
በቭላድሚር ፑቲን የቤጂንግ ጉብኝት የተፈረመውን የብዙ-ዋልታ ዓለም መግለጫ አስመልክተው በሰጡት አስተያየት፤ ዓለም የነጠላ-ዋልታ ሥርዓት መዞችን እንደቀመሰች አንስተዋል።
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዓለም በሁለት ጎራ ትመራ በነበረበት ወቅት የጥንካሬው ከፍታ ላይ ደርሶ የነበረ ቢሆንም፤ አንድ ወገን የበላይ በሆነበት ሥርዓት ውስጥ ግን እየተዳከመ መምጣቱን አጽንዖት ሰጥተዋል።
“ዓለም በአንድ ዋልታ ሥርዓት ዘመን እንዳየችው በርካታ ግጭቶችን አስተናግዳ አታውቅም" ሲሉም ባለሙያው አስረድተዋል።
ለዚህ የነጠላ-ዋልታ ዘመን አለመረጋጋት ማሳያ ናቸው ያሏቸውን የዩጎዝላቪያ፣ የሱዳን እና የኢትዮጵያን መከፋፈል እንዲሁም በሶማሊያ የነበረውን ጦርነት በምሳሌነት ጠቅሰዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X