ኢትዮጵያ በዜጎቿ ላይ እየደረሰ ያለውን ጥቃት የሚከታተል ልዑክ ወደ ደቡብ አፍሪካ እንደምትልክ አስታወቀች
12:59 21.05.2026 (የተሻሻለ: 13:04 21.05.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ በዜጎቿ ላይ እየደረሰ ያለውን ጥቃት የሚከታተል ልዑክ ወደ ደቡብ አፍሪካ እንደምትልክ አስታወቀች
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ በህንድ ከተካሄደው የብሪክስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ ጎን ለጎን፤ ከደቡብ አፍሪካ አቻቸው ሮናልድ ላሞላ ጋር ኢትዮጵያውያን ላይ እየደረሱ ያሉ ችግሮችን በጋራ መፍታት በሚቻልባቸው መንገዶች ዙሪያ መወያየታቸውን፤ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነቢያት ጌታቸው በሳምንታዊ መግለጫቸው አስታውሰዋል።
የሁለቱ ሀገራት ተቋማት የኢትዮጵያውያንን ደህንነት ለማረጋገጥ እና መሰል ጥቃቶችን ለመግታት በጋራ ለመሥራት ተስማምተዋል መባሉን ጠቅሶ የስፑትኒክ አፍሪካ ዘግቧል።
ይህንኑ ተከትሎ ጉዳዩን የሚከታተል እና ለጋራ መፍትሄ የሚሠራ የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን ወደ ደቡብ አፍሪካ እንደሚንቀሳቀስ ታውቋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X