አፍሪካ የመጪውን ግዜ የብሪክስ ኢኮኖሚዎች ችላ ማለት አትችልም - ደቡብ አፍሪካዊ ባለሙያ
09:04 21.05.2026 (የተሻሻለ: 09:14 21.05.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
አፍሪካ የመጪውን ግዜ የብሪክስ ኢኮኖሚዎች ችላ ማለት አትችልም - ደቡብ አፍሪካዊ ባለሙያ
"ብሪክስ አሁን ላይ በዋናነት በንግድ፣ በሸቀጦች እና በአገልግሎቶች ላይ ያተኮረ የኢኮኖሚ ጥምረት ቢሆንም፤ የደህንነት ስምምነቶች "በቀጣይ እንደሚከተሉ" የዲፕሎማሲ እና የአመራር ማዕከል ከፍተኛ የምርምር ባልደረባ ኦስካር ቫን ሄርደን ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
"በቻይና እና በሩሲያ መካከል ያለው ግንኙነት በጠነከረ ቁጥር ለብሪክስ የተሻለ ይሆናል፤ ለደቡባዊውም ዓለም ወሳኝ ነው" ሲሉ ባለሙያው ተናግረዋል።
ቻይና "አፍሪካን እንደ ስልታዊ አጋር" ትመለከታለች፤ ሩሲያ ደግሞ "በአፍሪካ ትልቅ አሻራ እንዲኖራት" ትፈልጋለች።
እንደ ቫን ሄርደን ገለጻ፤ ቻይና ከአፍሪካ ጋር በመሠረተ ልማት ግንባታ፣ ወደቦች፣ የፍጥነት ባቡር፣ የመንገድ አውታሮች፣ የአየር ማረፊያዎች እና ድልድዮች እንዲሁም በንግድ ልማት እየተባበረች ትገኛለች።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X