ብሪክስ ባለብዙ ዋልታ ዓለምን በመፍጠር ረገድ "ጉልህ እንቅስቃሴ እያደረገ ነው" - ኢትዮጵያዊ ባለሙያ

ሰብስክራይብ

ብሪክስ ባለብዙ ዋልታ ዓለምን በመፍጠር ረገድ "ጉልህ እንቅስቃሴ እያደረገ ነው" - ኢትዮጵያዊ ባለሙያ

"በአሁኑ ወቅት ብሪክስ እጅግ ከፍተኛ የሆነውን የዓለም ሕዝብ ቁጥር ያቀፈ ቢሆንም ይህን የሕዝብ ቁጥር ወደ ውጤት ለመቀየር" ግን ወሳኝ የሆኑ የውስጥ ሥራዎች እንደሚጠበቁ ከፍተኛ የምጣኔ ሀብት ባለሙያ እና የፖለቲካ ተንታኝ ሸዋፈራው ሽታሁንለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

በባለብዙ ዋልታ ዓለም ውስጥ ተጠቃሚ መሆን የሚቻለው "የአንድ ሀገር ምርቶችና አገልግሎቶች በሌላው ዓለም ዘንድ ተፈላጊ መሆን ሲችሉ" እና በተመሳሳይ መልኩ ሀገሪቱ "የሌሎች ሀገራትን ምርቶችና አገልግሎቶች ስትጠቀም" መሆኑን ሽታሁን አስረድተዋል።

"ይሁን እንጂ ጥቅም እውን እንዲሆን እና ግብይቶች በተግባር እንዲከናወኑ መጀመሪያ ራሳችንን ከውስጥ ማጠናከር ይኖርብናል" ብለዋል።

​ የሩሲያ ፕሬዚዳንት በቻይና ያደረጉትን ጉብኝት ተከትሎ መሪዎቹ የባለብዙ ዋልታ ዓለም ምሥረታ መግለጫን በጋራ ፈርመዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0