- Sputnik አፍሪካ, 1920
Continental Drift
በአፍሪካ ቅርፅ እየቀየሩ ያሉትን እንደዚሁም የደቡባዊውን ዓለም ክፍል ሚና በአዲስ መልክ እየገለጹ ያሉትን ስር ነቀል ለውጦች የሚቃኝ ፕሮግራም ነው። ትዕይንቱ ፖሊሲዎች፣ ገበያዎች እና ፈጠራዎች ከዕለት ተዕለት ሕይወት ጋር እንዴት እንደሚገናኙ በመመርመር በእውነታ ላይ የተመሰረቱ ግንዛቤዎችን እና ትክክለኛ የአፍሪካ አመለካከቶችን ያቀርባል።

ከምዕራባውያን ተጽዕኖ ባሻገር፦ የፑቲን እና ሺ ጂንፒንግ ስብሰባ የአፍሪካን ሉዓላዊነት እንዴት ይቀርጻል?

ከምዕራባውያን ተጽዕኖ ባሻገር፦ የፑቲን እና ሺ ጂንፒንግ ግንኙነት የአፍሪካን ሉዓላዊነት እንዴት ይቀርጻል?
ሰብስክራይብ
"የቭላድሚር ፑቲን የቻይና ጉብኝት የዓለም ሥርዓት ከአንድ ዋልታ ወደ ባለብዙ-ዋልታ እየተቀየረ መሆኑን ካሳዩ ግልጽ ማረጋገጫዎች አንዱ ነው። ይህ ጉብኝት የምዕራባውያን አገራት በዓለም መድረክ ላይ የነበራቸው የበላይነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ መምጣቱን የሚያሳይ ግልጽ ምልክት ነው" ሲሉ ሙሉዓለም ኃይለማርያም በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህር ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡
በዛሬው የኮንቲነንታል ድሪፍት ዝግጅታችን ሁለት አበይት ጉዳዮችን ይዘንላችሁ ቀርበናል ፤ የፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን የቤጂንግ ጉብኝት እና ለአፍሪካ የሉዓላዊነት ጉዞ የሚኖረው ስትራቴጂካዊ ትርጉም ከዓለም አቀፍ ግንኙነት ምሁሩ ሙሉዓለም ኃይለማርያም ጋር ተናግረዋል። ኢትዮጵያ ወደ መካከለኛው ምስራቅ የምታደርገውን የስጋ ኤክስፖርት በከፍተኛ አቅም ዳግም መጀመሯ እና የተከፈተው አዲስ የ"ግመል ስጋ" ገበያ ከአላና ግሩፕ ኢትዮጵያ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኸሊፋ ሁሴን ጋር ተወያይተዋል።
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ፡

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple PodcastsDeezerSpotifyAfripods Pocket CastsPodcast AddictCastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0