በመጪው ክረምት የማዕከላዊ፣ ሰሜን ምሥራቅ እና ሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ አካባቢዎች ከመደበኛ በታች ዝናብ እንደሚያገኙ ተተነበየ
19:46 20.05.2026 (የተሻሻለ: 19:54 20.05.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
በመጪው ክረምት የማዕከላዊ፣ ሰሜን ምሥራቅ እና ሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ አካባቢዎች ከመደበኛ በታች ዝናብ እንደሚያገኙ ተተነበየ
የምስራቅ አፍሪካ በይነ መንግሥታት የአየር ትንበያ ማዕከል ባወጣው መግለጫ፤ ከሰኔ እስከ መስከረም 2019 ዓ.ም ባለው የክረምት ወቅት አብዛኛዎቹ የአፍሪካ ቀንድ አካባቢዎች ከተለመደው በታች የሆነ ዝቅተኛ ዝናብ እና ከፍተኛ ሙቀት እንደሚጠብቃቸው ገልጿል።
ይህ የአየር ሁኔታ በተለይ በኢትዮጵያ፣ በደቡብ ሱዳን፣ በሱዳን፣ በኡጋንዳ፣ በጅቡቲ፣ በኤርትራ እና በኬንያ የአርሶ አደሩን ህይወት፣ የምግብ ዋስትና፣ የውሃ አቅርቦትን እንዲሁም የኃይል ማመንጫዎችን በእጅጉ ሊጎዳ እንደሚችል ተነግሯል።
የዘንድሮው የአየር ንብረት ሁኔታ ከፍተኛ ድርቅ እና አስከፊ የአየር መዛባት ከታየባቸው የ1990 እና 2015 የኤልኒኖ ዓመታት ጋር ተመሳሳይነት አለው ተብሏል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X