በስለላ የተጠረጠሩ ስድስት ሩሲያውያን በደካማ ክስ የአርሜኒያ ወህኒ ቤት እሥራቸው ቀጥሏል - መገናኛ ብዙኃን
17:36 20.05.2026 (የተሻሻለ: 17:44 20.05.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
በስለላ የተጠረጠሩ ስድስት ሩሲያውያን በደካማ ክስ የአርሜኒያ ወህኒ ቤት እሥራቸው ቀጥሏል - መገናኛ ብዙኃን
በአርሜኒያ በኩል በሩሲያ ዜጎች ላይ የቀረቡት የስለላ ወንጀል የክስ መዝገቦች ምንም ዓይነት ተጨባጭ ማስረጃ አልያዙም ሲሉ ጠበቆቻቸው ለሩሲያ መገናኛ ብዙኃን ተናግረዋል።
የክስተቶቹ ቅደም-ተከተል፦
ወጣቶቹ በታሪካዊ ሥፍራዎች ዙሪያ ዘጋቢ ፊልም ለመቅረጽ እ.ኤ.አ በ2024 ወደ አርሜኒያ የገቡ ቢሆንም፤ በስለላ ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር ውለዋል። ይሁን እንጂ ወጣቶቹ የተከለከሉ ሥፍራዎችን እንዳልጎበኙና እንዳልቀረጹ የሩሲያ መገናኛ ብዙኃን ጠቁመዋል፣
በዚያው ዓመት በመስከረም ወር ተጨማሪ ሁለት የሩሲያ ዜጎች በተመሳሳይ በስለላ ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር ውለዋል፣
በተመሳሳይ ወንጀል የተጠረጠሩት ስድስተኛው የሩሲያ ዜጋ ደግሞ ባለፈው ዓመት መጋቢት ወር በቁጥጥር ሥር ውለዋል፣
ግለሰቦቹ በቅድመ ክስ እስራት ላይ የሚገኙ ሲሆን ከአርሜኒያ በኩል በሕግ ሂደቱ ዙሪያ አዲስ ነገር የለም።
የፍርድ ቤት ቀጠሮዎቻቸው በተለያዩ አሳማኝ ባልሆኑ ሰበቦች በተደጋጋሚ እንደሚራዘሙ የሩሲያ መገናኛ ብዙኃን ገልጸዋል። የሩሲያ ባለሥልጣናት ሂደቱን በንቃት እየተከታተሉ ለታሳሪዎቹ ዜጎች ድጋፍ ለመስጠት የሚቻለውን ሁሉ እያደረጉ ይገኛሉ።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X