ሞዛምቢክ በካቦ ዴልጋዶ የተሠማራውን የሩዋንዳ ወታደራዊ ኃይል ለማስቀጠል የገንዘብ ድጋፍ አገኘች

© telegram sputnik_ethiopiaሞዛምቢክ በካቦ ዴልጋዶ የተሠማራውን የሩዋንዳ ወታደራዊ ኃይል ለማስቀጠል የገንዘብ ድጋፍ አገኘች
ሞዛምቢክ በካቦ ዴልጋዶ የተሠማራውን የሩዋንዳ ወታደራዊ ኃይል ለማስቀጠል የገንዘብ ድጋፍ አገኘች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 20.05.2026
ሰብስክራይብ

ሞዛምቢክ በካቦ ዴልጋዶ የተሠማራውን የሩዋንዳ ወታደራዊ ኃይል ለማስቀጠል የገንዘብ ድጋፍ አገኘች

​ የሁለቱ መንግሥታት ትብብር ስኬታማ እንደነበር እና ሞዛምቢክ የሩዋንዳ የደህንነት ኃይሎች በግዛቱ እያደረጉት ላለው ቀጣይነት ያለው ድጋፍ ትልቅ አድናቆት እንዳላት የሩዋንዳ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦሊቪዬ ንዱሁንጊሬሄ ተናግረዋል።

​ኪጋሊ፤ ከአውሮፓ ኅብረት እርዳታ ለማግኘት ያቀረበቻቸው ሁለት ጥያቄዎች ከብራሰልስ እምቢተኝነት እንደገጠማቸው እና አንዳንድ የኅብረቱ አባል ሀገራት ጉዳዩን ፖለቲካዊ እንዳደረጉት የገለጹት ሚኒስትሩ፤ ይህም "ለሞዛምቢክ ሕዝብ ሊደረግ የሚገባውን ወሳኝ ድጋፍ በሩዋንዳ ላይ ወደሚሰነዘር መሠረተ ቢስ ትችት ቀይሮታል" ሲሉ አክለዋል።

 

"​በዚህም ምክንያት በዚህ ዓመት ሩዋንዳ ወደ መሠረታዊው አካሄድ በመመለስ ከሞዛምቢክ መንግሥት ጋር ብቻ ቀጥተኛ ግንኙነት ለማድረግ ስትወስን፤ የሞዛምቢክ መንግሥት በበኩሉ በካቦ ዴልጋዶ ለሚገኙት የሩዋንዳ የደህንነት ኃይሎች የሚያስፈልገውን የገንዘብ ድጋፍ ያገኘ ሲሆን ወደፊትም ማረጋገጡን ይቀጥላል" ሲሉ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ላይ ባሠፈሩት ጽሑፍ ጠቁመዋል።

​በነዳጅ እና በተፈጥሮ ጋዝ በበለፀገው ግዛት የተካረረውን የጂሃዲስት አማፂያን ጥቃት ለመከላከል ነበር በሞዛምቢክ መንግሥት ጥያቄ መሠረት የሩዋንዳ የደህንነት ኃይሎች እ.ኤ.አ በ2021 በካቦ ዴልጋዶ የተሠማሩት።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0