ኢትዮጵያ በባህላዊ ሕክምና ዘርፍ ለተሰማሩ ማኅበራት ብሔራዊ ፌዴሬሽን አቋቋመች
19:29 19.05.2026 (የተሻሻለ: 19:34 19.05.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ በባህላዊ ሕክምና ዘርፍ ለተሰማሩ ማኅበራት ብሔራዊ ፌዴሬሽን አቋቋመች
ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ የባህላዊ ሕክምና አገልግሎትን ይበልጥ ለማዘመን፣ ቁጥጥር ለማድረግና ቅንጅትን ለማጠናከር በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚገኙ የባህላዊ ሕክምና ባለሙያዎች ማኅበራትን በአንድነት የሚያሰባስብ መሆኑ ተገልጿል።
የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የዘርፉ ተዋናዮችና ከ9 ክልሎች የተወጣጡ የማኅበራት ተወካዮች በተገኙበት ጠቅላላ ጉባኤ የፌዴሬሽኑ ረቂቅ መተዳደሪያ ደንብ በሙሉ ድምፅ ፀድቋል፡፡
አዲሱ ፌዴሬሽን የዓለም ጤና ድርጅት ያወጣውን የ2025-2034 ዓለም አቀፍ የባህላዊ ሕክምና ስትራቴጂ መሠረት በማድረግ፣ ባህላዊ ሕክምናን ከዘመናዊው የጤና ሥርዓት ጋር ለማቀናጀት ትልቅ ሚና ይጫወታል ተብሎ ይጠበቃል።
የሀገር በቀል የእፅዋት መድኃኒት አቅራቢዎች የተሳተፉበት የሰኔ 2016 ዓ.ም. የሀገር ውስጥ የህክምና ግብዓት ምርት እና ኢኖኔሽን ዐውደ-ርዕይ
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X