ሩሲያ እና ዚምባብዌ ወንጀልን ለመዋጋት የሚያስችሉ ሦስት የፍትሕ ስምምነቶችን ተፈራረሙ
18:28 19.05.2026 (የተሻሻለ: 18:34 19.05.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ሩሲያ እና ዚምባብዌ ወንጀልን ለመዋጋት የሚያስችሉ ሦስት የፍትሕ ስምምነቶችን ተፈራረሙ
የተድረገው ይፋዊ የኦንላይን የፊርማ ሥነ-ሥርዓት በሁለቱ አገራት መካከል ላለው የሁለትዮሽ የሕግ ትብብር አዲስ ምዕራፍ የከፈተ መሆኑን የሩሲያ ፍትሕ ሚኒስቴር አስታውቋል።
ሁለቱ ወገኖች የሚከተሉትን ሦስት ዓለም አቀፍ ስምምነቶች ተፈራርመዋል፡፡
የእስራት ፍርደኛ ግለሰቦች ቅጣታቸውን እንዲፈጽሙ ማዛወር፣
በወንጀል ጉዳዮች ላይ የጋራ የሕግ ድጋፍ ማድረግ እና
በዓለም አቀፍ የፍትሕ ዘርፍ ከሚፈጸሙ በደሎች (ያለአግባብ መጠቃቶች) ዜጎችን በጋራ መጠበቅን ናቸው።
የተፈረሙት ሰነዶች በሩሲያ እና በዚምባብዌ የፍትሕ እና የሕግ አስከባሪ አካላት መካከል ለሚኖረው ትብብር መሠረት የሚጥሉ መሆናቸውን የገለጸው ሚኒስቴሩ፤ ተከሳሾችም ቅጣታቸውን በዜግነት አገራቸው ውስጥ እንዲያሳልፉ ዕድል የሚሰጥ መሆኑን ጠቁሟል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

1/2
© telegram sputnik_ethiopia

2/2
© telegram sputnik_ethiopia
1/2
© telegram sputnik_ethiopia
2/2
© telegram sputnik_ethiopia