ኢትዮጵያ የወጪ ንግዷን የሚመራ አዲስ ብሔራዊ ባለሥልጣን ከምርጫ ማግሥት ልታቋቁም ነው
17:25 19.05.2026 (የተሻሻለ: 17:34 19.05.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ የወጪ ንግዷን የሚመራ አዲስ ብሔራዊ ባለሥልጣን ከምርጫ ማግሥት ልታቋቁም ነው
የሀገሪቱ መንግሥት የወጪ ንግድ ዘርፉን በተቀናጀና በተሳለጠ መልኩ ለመምራት የሚያስችል ራሱን የቻለ አዲስ ባለሥልጣን ለማቋቋም ማቀዱን የሀገር ውስጥ የግል ሚዲያ ለጉዳዩ ቅርበት ካላቸው ምንጮች መስማቱን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡
ባለሥልጣኑ ምርጫን ተከትሎ ከሚከናወነው አዲስ የመንግሥት ምሥረታ በኋላ ተግባራዊ እንደሚሆን የተገለፀ ሲሆን የማቋቋሚያ ረቂቅ ሐሳቡ ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት መቅረቡ ታውቋል።
በአሁኑ ወቅት የዘርፉ አመራርና ቁጥጥር በንግድና ቀጣናዊ ትስስር፣ በግብርና፣ በማዕድን፣ በኢንዱስትሪ እና በውኃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሥር ተበታትኖ መገኘቱ ለዘርፉ መዳከም እንደ ዋና ምክንያት ተጠቅሷል፡፡
ዘርፉን በዓለም አቀፍ ገበያ ተወዳዳሪ ለማድረግ እንደ ቀድሞው "የኢትዮጵያ የውጪ ንግድ ማስፋፊያ ኤጀንሲ" ተጠሪነቱ በቀጥታ ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የሆነ ነፃ ተቋም መፍጠር ግድ ማለቱ ተመላክቷል፡፡
ከማኅበራዊ ሚዲያ የተገኘው ቪዲዮ የሞጆ ደረቅ ወደብን ያሳያል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X