የኢትዮጵያን የምርጫ ሂደቶች ከዲጂታል ማጭበርበርና ከጥላቻ ንግግሮች ለመጠበቅ የሚያስችል ብሔራዊ መድረክ ሊቋቋም ነው

© telegram sputnik_ethiopiaየኢትዮጵያን የምርጫ ሂደቶች ከዲጂታል ማጭበርበርና ከጥላቻ ንግግሮች ለመጠበቅ የሚያስችል ብሔራዊ መድረክ ሊቋቋም ነው
የኢትዮጵያን የምርጫ ሂደቶች ከዲጂታል ማጭበርበርና ከጥላቻ ንግግሮች ለመጠበቅ የሚያስችል ብሔራዊ መድረክ ሊቋቋም ነው - Sputnik አፍሪካ, 1920, 19.05.2026
ሰብስክራይብ

የኢትዮጵያን የምርጫ ሂደቶች ከዲጂታል ማጭበርበርና ከጥላቻ ንግግሮች ለመጠበቅ የሚያስችል ብሔራዊ መድረክ ሊቋቋም ነው

የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ-መንግሥታት ድርጅት (ኢጋድ) የቅድመ ማስጠንቀቂያና ምላሽ ዘዴ ከአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን፣ ከተባበሩት መንግሥታት እና ከተመድ የልማት ፕሮግራም ጋር በመተባበር በኢትዮጵያ የጥላቻ ንግግርና የሀሰት መረጃዎችን ለመከላከል የሚያስችል ባለብዙ ተቋማት የጋራ መድረክ ለማቋቋም የሚያግዝ ብሔራዊ ስብሰባ እያካሄደ ይገኛል።

ይህ አዲስ ብሔራዊ መድረክ የመንግሥት ተቋማትን፣ የምርጫ አስፈጻሚ አካላትን፣ የፖለቲካ ፓርቲዎችን፣ መገናኛ ብዙኃንን፣ የሲቪል ማኅበራትንና የቴክኖሎጂ ባለሙያዎችን በአንድነት የሚያገናኝ መሆኑን ኢጋድ አስታውቋል፡፡

  በተለይም በምርጫ ወቅት የሚሰራጩ የተዛቡ ምስሎች፣ የተቀየሩ የዜና ርዕሶችና የሀሰት መረጃዎች ማኅበራዊ ትስስርንና ዲሞክራሲያዊ ሂደቶች ላይ የሚፈጥሩትን ተጽዕኖ አስቀድሞ ለመከላከልና የተቀናጀ ምላሽ ለመስጠት እንደሚያገለግል ተገልጿል።

 

የጋራ መድረኩ በኢትዮጵያና በደቡብ ሱዳን የምርጫ ወቅቶች የሀሰት ትርክቶችን የመከታተልና የመቀነስ ተግባራዊ መሣሪያዎችን በሙከራ ደረጃ በመተግበር ከምርጫ ባሻገርም የማኅበራዊ ትስስርንና የፖሊሲ ቀረጻን ለማገዝ ታስቦ የተዘጋጀ ነው።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0