https://amh.sputniknews.africa/20260519/4048219.html
“የኒውክሌር ኃይል ለኢትዮጵያ የህልውና ጉዳይ ነው” የኢትዮጵያ ኒውክሌር ኃይል ምክትል ኮሚሽነር
“የኒውክሌር ኃይል ለኢትዮጵያ የህልውና ጉዳይ ነው” የኢትዮጵያ ኒውክሌር ኃይል ምክትል ኮሚሽነር
Sputnik አፍሪካ
“የኒውክሌር ኃይል ለኢትዮጵያ የህልውና ጉዳይ ነው” የኢትዮጵያ ኒውክሌር ኃይል ምክትል ኮሚሽነር ሽፈራው ተሊላ፣ የኒውክሌር ኃይል ለኢትዮጵያ የቅንጦት ምርጫ ሳይሆን ከቀን ወደ ቀን እያደገ የመጣውን የኃይል ፍላጎት ለማሟላትና ዘላቂ የኢንዱስትሪ... 19.05.2026, Sputnik አፍሪካ
2026-05-19T15:21+0300
2026-05-19T15:21+0300
2026-05-19T15:24+0300
sputnik africa
telegram sputnik_ethiopia
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/img/07ea/05/13/4047555_0:67:1280:787_1920x0_80_0_0_ef8056eaf95c8ea0dc0222e60d68e1fc.jpg
“የኒውክሌር ኃይል ለኢትዮጵያ የህልውና ጉዳይ ነው” የኢትዮጵያ ኒውክሌር ኃይል ምክትል ኮሚሽነር ሽፈራው ተሊላ፣ የኒውክሌር ኃይል ለኢትዮጵያ የቅንጦት ምርጫ ሳይሆን ከቀን ወደ ቀን እያደገ የመጣውን የኃይል ፍላጎት ለማሟላትና ዘላቂ የኢንዱስትሪ ሽግግር ለማምጣት የግድ የሚል የህልውና ጉዳይ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ "ሀገሪቱ ኢኮኖሚዋን ይበልጥ ለማሳደግ ለአየር ንብረት ተስማሚ በሆኑ ታዳሽ ኃይሎች ላይ ትኩረት አድርጋ እየሠራች ቢሆንም፣ የኢኮኖሚው ፈጣን እድገትና የኢንዱስትሪዎች መስፋፋት አስተማማኝና ከፍተኛ የኃይል አማራጭ መፈለግን አስገዳጅ አድርጎታል።" ብለዋል፡፡ የኢትዮጵያ ኒውክሌር ኢነርጂ ኮሚሽን ከዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ ጋር በመተባበር ለሀገሪቱ የወደፊት የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ የሚሆን ቦታን ለመምረጥና ለማጥናት የሚያስችል ብሔራዊ አውደ ጥናት ከግንቦት 10 እስከ 14 ቀን 2018 ዓ.ም ማካሄድ ጀምሯል። ኢትዮጵያ እና ሩሲያ በኢትዮጵያ የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ልማት ዙሪያ የድርጊት መርኃ-ግብር እና ስትራቴጂካዊ ፍኖተ ካርታ መፈራረማቸው ታወሳል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
Sputnik አፍሪካ
feedback.africa@sputniknews.com
+74956456601
MIA "Rossiya Segodnya"
2026
Sputnik አፍሪካ
feedback.africa@sputniknews.com
+74956456601
MIA "Rossiya Segodnya"
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
feedback.africa@sputniknews.com
+74956456601
MIA "Rossiya Segodnya"
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/img/07ea/05/13/4047555_72:0:1209:853_1920x0_80_0_0_bdca9d4899c93bdb1397285687cb5bf9.jpgSputnik አፍሪካ
feedback.africa@sputniknews.com
+74956456601
MIA "Rossiya Segodnya"
sputnik africa, telegram sputnik_ethiopia
sputnik africa, telegram sputnik_ethiopia
“የኒውክሌር ኃይል ለኢትዮጵያ የህልውና ጉዳይ ነው” የኢትዮጵያ ኒውክሌር ኃይል ምክትል ኮሚሽነር
15:21 19.05.2026 (የተሻሻለ: 15:24 19.05.2026) “የኒውክሌር ኃይል ለኢትዮጵያ የህልውና ጉዳይ ነው” የኢትዮጵያ ኒውክሌር ኃይል ምክትል ኮሚሽነር
ሽፈራው ተሊላ፣ የኒውክሌር ኃይል ለኢትዮጵያ የቅንጦት ምርጫ ሳይሆን ከቀን ወደ ቀን እያደገ የመጣውን የኃይል ፍላጎት ለማሟላትና ዘላቂ የኢንዱስትሪ ሽግግር ለማምጣት የግድ የሚል የህልውና ጉዳይ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
"ሀገሪቱ ኢኮኖሚዋን ይበልጥ ለማሳደግ ለአየር ንብረት ተስማሚ በሆኑ ታዳሽ ኃይሎች ላይ ትኩረት አድርጋ እየሠራች ቢሆንም፣ የኢኮኖሚው ፈጣን እድገትና የኢንዱስትሪዎች መስፋፋት አስተማማኝና ከፍተኛ የኃይል አማራጭ መፈለግን አስገዳጅ አድርጎታል።" ብለዋል፡፡
የኢትዮጵያ ኒውክሌር ኢነርጂ ኮሚሽን ከዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ ጋር በመተባበር ለሀገሪቱ የወደፊት የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ የሚሆን ቦታን ለመምረጥና ለማጥናት የሚያስችል ብሔራዊ አውደ ጥናት ከግንቦት 10 እስከ 14 ቀን 2018 ዓ.ም ማካሄድ ጀምሯል።
ኢትዮጵያ እና ሩሲያ በኢትዮጵያ የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ልማት ዙሪያ የድርጊት መርኃ-ግብር እና ስትራቴጂካዊ ፍኖተ ካርታ መፈራረማቸው ታወሳል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X


