ባለፉት ሦስት ዓመታት 17,508 አዳዲስ ትምህርት ቤቶች ተገንብተዋል - የገቢዎች ሚኒስቴር

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ባለፉት ሦስት ዓመታት 17,508 አዳዲስ ትምህርት ቤቶች ተገንብተዋል - የገቢዎች ሚኒስቴር
የገቢዎች ሚኒስቴር ከብሔራዊ ታክስና ግብር የሚገኙ ገቢዎች ለሀገር በቀል የመሠረተ ልማት ግንባታዎች እያበረከቱት ያለውን አስተዋጽኦ በአኃዝ አስደግፎ ይፋ አድርጓል።
እንደ ሚኒስቴሩ ገለፃ በግብር ገቢው የተከናወኑ ሌሎች ዋና ዋና መሠረተ ልማቶች፦
🟠 ንጹህ መጠጥ ውሃ፦ በ2017 ዓ.ም ሀገራዊ የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ሽፋን 72.65 በመቶ የደረሰ ሲሆን፣ ባለፉት 9 ወራት ብቻ 2.75 ሚሊዮን ተጨማሪ ዜጎች ተጠቃሚ ሆነዋል።
🟠 የደመወዝ ድጎማ፦ ባለፉት ዘጠኝ ወራት 113 ቢሊዮን ብር የደመወዝ ድጎማ ተደርጓል።
🟠 የስፖርት መሠረተ ልማት፦ የባህር ዳር፣ አርባ ምንጭ፣ ድሬዳዋ (99.7 በመቶ) እንዲሁም የአቃቂ (91 በመቶ) ስታዲየሞች ተገንብተዋል። የአደይ አበባ ብሔራዊ ስታዲየም ግንባታም እየተከናወነ ይገኛል።
🟠 የኃይል አቅርቦት፦ ባለፉት ሰባት ዓመታት ከ15 ሚሊዮን በላይ አዳዲስ ዜጎች የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ መሆን ችለዋል።
🟠 የኮሪደር ልማት፦ የከተማና የገጠር የኮሪደር ልማት ሥራዎች በስፋት እየተሰሩ ይገኛሉ።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X