የሩሲያ ፕሬዝዳንት ለሁለትዮሽ ውይይት እና ለትምህርት ዓመታት ማስጀመሪያ የቻይናን ጎብኝት
08:30 19.05.2026 (የተሻሻለ: 08:34 19.05.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የሩሲያ ፕሬዝዳንት ለሁለትዮሽ ውይይት እና ለትምህርት ዓመታት ማስጀመሪያ የቻይናን ጎብኝት
ስለ ጉብኝቱ ዐቢይ እውነታዎች፦
🟠 ፑቲን እ.አ.አ. ከ2000 ጀምሮ፣ በመንግሥታዊ እና በይፋዊ ጉብኝቶች እንዲሁም በቀበቶ እና መንገድ (ቤልት ኤንድ ሮድ) መድረኮች፣ በኦሊምፒክ፣ በሻንጋይ ትብብር ድርጅት፣ በእስያ–ፓሲፊክ የኢኮኖሚ ትብብር፣ በብሪክስ ጉባኤዎች እና በድል ሰልፎች ላይ በመሳተፍ ቻይናን 20 ጊዜ ጎብኝተዋል፡፡
🟠 በዚህ ጉብኝታቸው አጀንዳ ላይ የተካተቱ ጉዳዮች፦ ኢነርጂ፣ የሕዋ ትብብር፣ የኢኮኖሚ ጉዳዮች እና ዓለም አቀፍ ግንኙነቶችን ማረጋጋት፤
🟠 ጉብኝቱ፣ ከቻይናው ፕሬዝዳንት ጋር የሚደረጉ ውይይቶችን እንዲሁም የሩሲያ-ቻይና የትምህርት ዓመታት (2026–2027) የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓትን ያካትታል፡፡
🟠 የጋራ መግለጫ እና በርካታ የሁለትዮሽ ሰነዶች ይፈረማሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
🟠 የሩሲያው ልዑክ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሮችን፣ ሚኒስትሮችን እና የንግድ መሪዎችን ያካተተ ነው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X