ጋና ለአፍሪካ የጤና ሉዓላዊነት ትሟገታለች - ፕሬዝዳንት

ሰብስክራይብ

ጋና ለአፍሪካ የጤና ሉዓላዊነት ትሟገታለች - ፕሬዝዳንት

በከፍተኛ የገንዘብ ድጋፍ ቅነሳ ምክንያት ዓለም አቀፍ የጤና ዕርዳታ በ40 በመቶ ማሽቆልቆሉን ጆን ድራማኒ ማሃማ አጽንኦት ሰጥተው ገልጸዋል።

የአሜሪካ የዕርዳታ ፕሮግራሞች መታገዳቸውን ተከትሎ ጋና ወደ 180 ሚሊዮን ዶላር ገደማ ማጣቷን ጠቁመዋል።

ሆኖም እ.ኤ.አ. ከ2025 ጀምሮ ተግባራዊ እየተደረገ የሚገኘው የ“አክራ ሪሴት” የጤና ፕሮግራም፤ የአገር ውስጥ ሀብቶች የቀድሞውን በለጋሾች ላይ ጥገኝነት የመሆን ሥርዓት መተካት እንደሚችሉ ማሳያ መሆኑን የጋናው ፕሬዝዳንት ተናግረዋል።

በሀገሪቱ መሪ ይፋ የተደረገው ይህ ፕሮጀክት በሦስት ዋና ዋና ምሰሶዎች ላይ ያረፈ ነው፡፡

ማሻሻያዎችን የማቅረብ ኃላፊነት የተጣለበት ገለልተኛ አማካሪ፣

የዋና ዋና ዓለም አቀፍ የጤና ተቋማትን ስትራቴጂዎች ለማስማማት የሚሠራ የቅንጅት ታዛቢ ማዕከል፣

የሀገር ውስጥ ምርትን እና የባዮ-ኢኖቬሽን ሥራዎችን በገንዘብ ለመደገፍ የሚያስችል አሠራር።

እነዚህ መግለጫዎች የተሰጡት ከግንቦት 10 እስከ 15 በጄኔቫ ስዊዘርላንድ እየተካሄደ በሚገኘው 79ኛው የዓለም ጤና ጉባኤ ላይ ነው።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0