- Sputnik አፍሪካ, 1920
The Rising South
የዓለም አቀፍ የኃይል ሚዛን እየተቀየረ ባለበት በዚህ ወቅት - ኢትዮጵያን፣ አፍሪካን እና ሌሎችን የሚቀርጹ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ እና የማህበራዊ ሃይሎች ወደምንመለከትበት ወደ “ራይዚንግ ሳዉዝ” እንኳን በደህና መጡ፡፡ ደቡባዊ አመለካከቶችን ወደ ዓለም አቀፋዊ ውይይት መድረክ ስናቀርብ የአሰላሳዮችን ፣ የመሪዎችን እና የለዉጥ ፈጣሪዎችን ሃሳብ ያድምጡ።

ከሰው ሰራሽ አስተውሎት ወደ የሰው ሰራሽ አጠቃላይ አስተውሎት ፡-የቴክኖሎጂው ግስጋሴ እና የኢትዮጵያ ዝግጁነት

ከሰው ሰራሽ አስተውሎት ወደ የሰው ሰራሽ አጠቃላይ አስተውሎት፡ የቴክኖሎጂው ግስጋሴ እና የኢትዮጵያ ዝግጁነት
ሰብስክራይብ
የሰው ሰራሽ አስተውሎት ፣ ወደ ሰው ሰራሽ አጠቃላይ አስተውሎት (AGI) በኋላ ወደ ሰው ሰራሽ ልዕለ አስተውሎት (ASI) እየገሰገሰ ነው፡፡ ማህበረሰባችን ለዚህ ታላቅ ለውጥ ምን ያህል ዝግጁ ነው?
"የሰው ሰራሽ አጠቃላይ አስተውሎት (AGI) ማለት በሁሉም ዘርፎች እንደ ሰው ማሰብና መስራት የሚችል ሲስተም ነው፤ አዲስ ቴክኖሎጂ ሲመጣ ፈርተን ጥግ የምናደርገው ሳይሆን፣ በጥንቃቄ ቃኝተን የምንጠቀምበት ሊሆን ይገባል። ሰው ሰራሽ አስተውሎትን ማምለክ ደረጃ ማድረስ የለብንም፤ ሚዛኑን እንዴት አድርገን እንደምንይዘው ማወቅ ግን ወሳኝ ነው።" ሲል የትረስቴክ አይቲ ሶሉሽንስ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ናታን ግርማ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግሯል፡፡
በዛሬው የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅታችን ሰው ሰራሽ አስተውሎት ዓለማችንን በምን መልኩ እየቀየረው ነው? እንደ ኢትዮጵያ ላሉ በማደግ ላይ ያሉ ሀገራት ምን ዓይነት ዕድሎችን ይዞ መጥቷል ? ስጋቶቹስ ምንድን ናቸው? በሚሉና ሌሎች ነጥቦች ዙሪያ ከትረስቴክ አይቲ ሶሉሽንስ (TrusTech IT Solutions) ዋና ስራ አስኪያጅ እና ባለሙያ አቶ ናታን ግርማ ጋር በጥልቀት ተወያይተናል።
ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ፡

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ : Apple PodcastsSpotifyDeezerAfripodsPodcast AddictPocket CastsCastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0