- Sputnik አፍሪካ, 1920
Continental Drift
Continental Drift' በአፍሪካ ቅርፅ እየቀየሩ ያሉትን እንደዚሁም የአለም የደቡብን ክፍል ሚና በአዲስ መልክ እየገለጹ ያሉትን ስር ነቀል ለውጦች የሚከታተል ፕሮግራም ነው።ትዕይንቱ ፖሊሲዎች፣ ገበያዎች እና ፈጠራዎች ከዕለት ተዕለት ሕይወት ጋር እንዴት እንደሚገናኙ በመመርመር በእውነታ ላይ የተመሰረቱ ግንዛቤዎችን እና ትክክለኛ የአፍሪካ አመለካከቶችን ያቀርባል።

የአፍሪካን የኢኮኖሚ አእምሮ ማን ይገነባዋል? ዕውቀት፣ ስፖርት እና አዲሱ የሉዓላዊነት ትግል

የአፍሪካን የኢኮኖሚ አእምሮ ማን ይገነባዋል? ዕውቀት፣ ስፖርት እና አዲሱ የሉዓላዊነት ትግል
ሰብስክራይብ
የአፍሪካ ሉዓላዊነት ጥያቄ ከማዕድን እና ከንግድ ኮሪደሮች ባለፈ፣ አህጉሪቱን የሚያስተዳድሩ መሪዎች በሚቀረጹበት የዕውቀት ሥርዓት ላይ ያተኩራል። በሌላ በኩል ደግሞ አዲስ አበባ የመጀመሪያውን አህጉራዊ የተራራ ብስክሌት ውድድር በማስተናገድ፣ ከተማን እንደ ዲፕሎማሲ እና የ'ሶፍት ፓወርን' መድረክነት እየተጠቀመችበት ትገኛለች።

"አፍሪካውያን የራሳቸውን ሥርዓተ-ትምህርት ማዘጋጀት አለባቸው። ይህም በጣም አስፈላጊ ነው። ሌላው ችግር በመካከላችን ጠንካራ አህጉራዊ ግንኙነት የለንም። ስለዚህ ይህንን ግንኙነት መገንባት አለብን። ይህ ጉባኤ የአፍሪካ ቢዝነስ ትምህርት ቤቶች በራሳቸው ችግሮች ላይ ተመሥርተው በጋራ እንዲሠሩ በማድረግ ረገድ ትልቅ ፋይዳ ይኖረዋል።" ሲሉ ደሳለኝ መኩሪያ ንጉሤ፣ የክቡር ኮሌጅ ፕሬዝዳንት ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡

በዛሬው የኮንቲነንታል ድሪፍት ዝግጅታችን፣ አፍሪካ የራሷን ተቋማት በራሷ ፍላጎት ላይ ተመሥርታ የመገንባት ስትራቴጂን ከሁለት እንግዶች ጋር እንፈትሻለን፦ ከክቡር ኮሌጅ ፕሬዝዳንት ደሳለኝ መኩሪያ ንጉሤ ጋር ስለ ቢዝነስ ትምህርት፣ አመራር እና ስለ ዕውቀት ሉዓላዊነት፤ ከኢትዮጵያ ብስክሌት ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ወዲሙ ኃይሌ ጋር ስለ ከተማ ስፖርት ዲፕሎማሲ እና ስለ አዲስ አበባ ገጽታ ግንባታ እንወያያለን።
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ ፡

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple PodcastsDeezerSpotifyAfripods Pocket CastsPodcast AddictCastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0